ከተጠቀሱት የተለያዩ መልካአምድራዊ ገጽታዎች ባሻገር ኢትዮጵያ በተለያዩ ጐድጓዳ ቦታዎች፣ ወንዞች፣ ሸለቆዎችና አስደናቂ መልከአምድሮች የታደለች አገር ናት፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉት ወንዞች ውስጥም አባይ (ጥቁር አባይ)፣ አዋሽ፣ ባሮ፣ ኦሞ፣ ተከዜ እንዲሁም ዋቢ ሸበሌ ይገኙበታል፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ ምቹ የአየር ሁኔታዎችን ያሏት አገር ስትሆን ከቀዝቃዛ እስከ መካከለኛ እንዲሁም ከመለስተኛ ትሮፓካል እስከ ትሮፓካል ያለው ሁሉ የሚገኝባት ባለፀጋ አገር ናት፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የአገሪቱ የአየር ሁኔታ በከፍተኛ ቦታዎች የአየር ሁኔታ ተጽእኖ ያለበት ሆና ይገኛል ምንም እንኳ አገሪቱ ከኢኩዌተር 150 ዲግሪ ብቻ ከፍ ብላ ብትገኝም፡፡ በአገሪቱ ሁለት የዝናብ ወቅቶች ይገኛሉ፡፡ ትንሽ ዝናብ የሚዘንብበት የየካቲት እና መጋቢት ወር እና ከፍተኛ ዝናብ የሚዘንብበት እስከ መስከረም ያለው ወቅት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መሠረታዊ የአየር ክልሎች፤ የትሮፒካል የዝናባማ የአየር ፀባይ፣ ደረቅ የአየር ፀባይ እና መለስተኛ ሞቃት ዝናባማ የአየር ፀባዩች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ 18 አግሮ ኢኮሎጂካል (Agro-ecological) ክልሎች እና ሶስት ዋና ዋና ተለምዶአዊ የአየር ፀባይ አይነቶች ሲኖሩ እነሱም አንደኛው ደጋ ማለትም ለስላሳ የከፍተኛ ቦታዎች የአየር ፀባይ ሲሆን ከ2,500 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ የሚገኝ የአየር ፀባይ ሁለተኛው ወይናደጋ ሲሆን መካከለኛ ሙቀት የአየር ፀባይ ሲሆን ከ 1500-እስከ 2500 የባህር ጠለል በላይ ባሉ አካባቢዎች የሚገኝ የአየር ፀባይ እና ሶስተኛዉ ቆላ የሚባለዉ በሞቃታማና ከባህር ጠለል በታች በ1,500 ሜትር ዝቅተኛ በሆኑ ቦታዎች የሚገኝ ሞቃት የአየር ፀባይ ነው፡፡

ሶስቱ የአየር ፀባይ አይነቶች ደግሞ ወደ ሌሎች የአየር ፀባይ አይነቶች ይከፋፈላሉ፡፡ ሁለቱ ጫፍ ላይ የሚገኙም እጅግ ሞቃት የአየር ፀባይ የሚገኝባቸውና አመታዊ የዝናብ መጠናቸውም ከ450 ሚ.ሜ በታች እና ከ270 ሴልሺየስ እሽከ 320 ሴልሺየስ የሆኑት እና ሌላኛው ደግሞ ቀዝቃዛ የከፍተኛ ቦታዎች የአየር ፀባይና ሞቃት በሆነ ወራት ከ100 ዴልቪየስ በታች የሆኑ ሞቃት ያላቸው እና አመታዊ የዝናብ መጠናቸው ግን ከ800-200 ሚ.ሜ የሆነ የአየር ፀባይ ያላቸው ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች በቡሄር እና በባህል ብዙ አይነት ናቸው፡፡ በአገሪቱ ከ80 በላይ ብሔሮች እና ብሄር ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ህዝቦችም በአጠቃላይ ከ80 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገራሉ በውስጣቸውም 22 ኩሸቲክ፣ 12 ሴሚቲክ እና 18 ኦሞቲክ እንዲሁም 18 ኒሎ ሳሐራን ቋንቋዎችን ይናገራሉ፡፡ አማርኛ የፌዴራል መንግስት የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ እንግሊዝኛ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በከፍተኛ ተቋሞች የማስተማሪያ ቋንቋ ነው በተጨማሪም በባንኮች እና በኢንሹራንሶችም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ ትሁት እና እንግዳ ተቀባይ ህዝቦች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ታማኞች፣ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸው፣ ተግባቢዎች እና ጠንካራ ሰራተኞች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢጣሊያዊው የታሪክ ሰው ኮንቲ ሮሲኒ በመጽሀፉ ሲጽፍ ኢትዮጵያውያን ሁሌም ጥሩ ስም ያላቸውን ሩህሩህ እንዲሁም ከመጠን በላይ ትሁት ናቸው ሲል ጽፏል፡፡

Pages: 1  2