ስለ ኢትዮጵያ

ኦፊሰላዊ መጠሪያ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን በዘጠኝ  ክልሎች የተዋቀረ ሲሆን እነርሱም ትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሊያ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ ጋምቤላ እንዲሁም የሀረሪ ክልላዊ መንግስትና የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ይገኙበታል፡፡ የብሔራዊ ክልላዊ መንግስቶችና ሁለቱ አስተዳደራዊ ካውንስል ከተሞች ደግሞ ወደ ስምንት መቶ ወረዳዎች (districts) እና ወደ 15,000 የሚጠጉ ቀበሌዎች (Lowest Level of elected administration) ይከፋፈላሉ፡፡

 

 ጂኦግራፊ እና ህዝብ

ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ በሆነ አቀማመጥ በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ በተለምዶ የአፍሪካ ቀንድ በሚባለው አቅጣጫ ለአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ኤዥያ አዋሳኝ መስቀለኛ በሆነ አቀማመጥ ተቀምጣ ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር 72.4 ሚሊዮን (2004?) ሲሆን ናይጄርያን እና ግብጽን በመከተል በአፍሪካ በሶስተኛነት ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ የካሬ ስፋጽ 1.14 ስኩዌር ኪ.ሜ (445,000 ስኩዌር ማይል) ሲሆን 58.9 ነዋሪዎች በአንድ ኪ.ሜ ስኩዌር ላይ ሰፍረው ይገኛሉ (2002)፡፡

ኢትዮጵያን የሚያዋስኗት አገራት ጂቡቲ እና ሶማሊያ በምስራቅ፣ ኤርትራ በሰሜን፣ ሱዳን በምዕራቡ፣ ኬንያ በደቡብ ናቸው፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ እና መካከለኛው ምስራቅን እና አውሮፓን ለሚያገናኙት ወደቦችም በቅርበት ትገኛለች፡፡ ለእነዚህ ወደቦች ያላት ቅርበትም የአገሪቱን አለም አቀፍ ንግድ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

በመልከ አምድር አቀማመጧ ኢትዮጵያ የተለያዩ ተቃራኒ የሆኑ ገጽታዎች ይገኙባታል፡፡ እጅግ ከፍታ ካለቸው ተራራዎች እና አምባዎች እስከ ግዙፍ ሸለቆዎች እና ዝቅተኛ ቦታዎች፣ ጠመዝማዛ ወንዞች እና ሐይቆች እንዲሁም የተዘረጉ ሜዳዎች ይገኙበታል፡፡ በአለም ዝቅተኛው ቦታ ከሆነው የደሎል ዝቅተኛ ቦታ ማለትም 148 ሜትር ከባህር ጠለል በታች እስከ በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ከሚገኘዉ ከፍተኛው የራስ ዳሽን ተራራ ጫፍ ማለትም 4620 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ የሆኑ መልከአ ምድሮችም ይገኙበታል፡፡ የአገሪቱን 56% የሚሆነውን አጠቃላይ ሽፋን የሚይዙት ከፍታማ (highlands) ቦታዎች በሰፋፊ ከ1000 ሜትሮች በላይ ዝቅ ብለው በሚገኙ (ዝቅተኛ Lowlands) ተከበው ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዋነኛ መልከ አምድራዊ ገጽታዎች አሁን ያላቸውን ምድራዊ ቅርጽ የያዙት ታላቁ የስምጥ ሸለቆን በፈጠሩት ግዙፍ እና አስደናቂ ጂኦግራፊያዊ የቮልካኖ ፍንዳታዎች ነዉ፡፡ በአፍሪካ አህጉር ምስራቃዊ ክፍል በተከሰቱ የመሬት መሠንጠቆች አማካኝነት የተፈጠሩ ናቸው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጦች የፈጠሩት ስምጥ ሸለቆ ከአፍሪካ ሰሜን ምስራቃዊ መጋጠሚያና ከምስራቃዊ የሜዴትራንያን ባህር ጀምሮ እስከ ደቡባዊ አፍሪካ ሞዛምቢክ የተዘረጋ ሆኖ ዛሬ ይገኛል፡፡

ከዚህም ጋር የተያያዙትን የኢትዮጵያ መሠረታዊ ገጽታዎች ከአፋር መልካአ ምድር ገጽታዎች ጀምረው ወደታች በሚታዩት ልዩ መልከአ ምድር ማስተዋል ይቻላል፡፡

በተጨማሪም በጊዜው የተከሰቱት የቮልካኖ ምልክቶችም በምዕራባዊዉ የድንበር መሬቶችም ይስተዋላሉ፡፡ ታላቁ ስምጥ ሸለቆ አገሪቱን ምዕራባዊ እና ምስራቃዊ ከፍተኛ ቦታዎች ብሎ የከፈለ ሲሆን ሌላው የአገሪቱ አስደናቂ መልከአምድራዊ ገጽታ ነው፡፡

Pages: 1  2