የአድዋ ድል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ህያው መሰረት መሆኑ ተገለጸ፤

የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል " በትላንቱ ትውልድ የተሠራና በዛሬው ትውልድ የተደገመ ከፍ ያለ ድል መሆኑን በመዘከር አሁን ያለችዋን አዲስቷን ኢትዮጵያ ትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆነች የማሳየትን" ዓላማ ሰንቆ "የአድዋ ድል ብዝሃነትን ላከበረች ኢትዮጵያ ድህነትን ለማሸነፍ የሚያስችል ህያው አብነት ነው" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶችና በሕዝባዊ ንቅናቄ በድምቀት እንደሚከበር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ።

Read More

የህዳሴ ግድብ የቦንድ ሳምንት በይፋ ተጀመረ፣

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ደንጋይ የተጣለበትን 6ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አገር አቀፍ ልዩ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት ተጀመረ።

Read More

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረሙ፤

ኢትዮጵያና ላይቤሪያ በሙያና ቴክኒክ ትምህርት፣ በጤናና ጤና ሳይንስ፣ በእንሰሳትና አሳ ሃብት ልማት እና በኢንዱስትሪ ልማት የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረሙ። ስምምነቶቹ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በአገራችን የሚያደርጉትን የ3 ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ የተደረጉ ናቸው።

Read More

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ፣

ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለተኛውን ዙር የሥራዓተ-ጾታ አካቶ ስልጠና እየሰጠ ነው፤

በውጭ ጉዳይ ሚስቴር የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት እና በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የስራዓተ-ጾታ ልማት ማዕከል ትብብር በመስሪያ ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ የስርዓተ-ጾታ አካቶን ለማስረጽ የሚያስችል ስልጠና ተካሄደ።

Read More

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በሶማሊያ የተደረገውን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር አደነቁ፤

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ ‘’Building Security in a post- conflict country: Beyond Guys and Guns in Somalia" በሚል አርዕስት በተደረገው ውይይት ሶማሊያን አስመልክቶ ሲናገሩ በሶማሊያ የተደረገው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚደነቅ ነው ብለዋል።

Read More

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጋር መከሩ፤

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ተወካይ እና ከአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሚስ ፌደሪካ ሞገህሪኒ ጋር መከሩ።

Read More

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ማሠልጠኛ ተቋም እና በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር MGIMO ዩኒቨርሲቲ መካከል የትብብር ስምምነት ተፈረመ፤

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ማሠልጠኛ ተቋም እና በሩሲያው Moscow State Institute of International Relations (MGIMO)ዩኒቨርሲቲ መካከል የመግባቢያ ሰነድ እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 17/2017 ሞስኮ ውስጥ ተፈርሟል።

Read More

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ለሙኒኩ የጸጥታ ጉባኤ ጀርመን ገቡ፤

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በ53ኛው የሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጀርመን ገብተዋል።

Read More

15ኛው የአፍሪካ ፋይን ኮፊ ስብሰባና አውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፤

15ኛው የአፍሪካ ፋይን ኮፊ ስብሰባና አውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

Read More