Back

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ፣

መጋቢት 26፣2009 ዓ.ም

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር መጋቢት 26፣2009 ዓ.ም ለ3 ቀናት ይፋዊ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደረገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ውይይት በማድረግ በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ሁለቱን አገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስምምነቶች ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡