Back

ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ላላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ

መጋቢት 26፣2009 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ ቆይታቸው ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጋና አምባሳደር የነበሩትን አልበርት ያንኪን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ላላት ታሪካዊ  ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትኩረት ትሰጣለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትሩ አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት በማጠናከር፣ለአፍሪካ የጋራ አጀንዳዎችና ፍላጎቶች በአህጉራትና በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠበቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቀርበውላቸዋል፡፡ሚኒስትሩ አክለው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማሳደግ ለሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ጥቅም መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የጋና አምባሳደር የሆኑት  አልበርት ያንኪን በበኩላቸው በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡አምባሳደሩ አክለው የኢትዮ-ጋና ግንኙነት በፓን አፍሪካ መርህ ላይ የተመሰረተ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን ተናግረው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተመረሙ ስምምነቶችን ወደ ተግባር በመቀየር ለጋራ ጥቅም መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡