ከአጎራባች ሀገራት ጋር የሚኖረን ግንኙነት

ከአጎራባች ሀገራት ማለትም ከሱዳን፣ ከኤርትራ ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከኬንያ ጋር የሚኖረን ግንኙት የተመሰረተው በመሰረታዊ አገራዊ ጥቅማችን እና ደህንነታችን ላይ ነው:: በመሆኑም ከነዚህ ሀገራት ጋር የሚኖረን ግንኙት የሚያጠነጥነው ለአገራቸን ልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ካላቸው ፋይዳ አንጻር ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ግምገማ መሰረት አጎራባች ሀገራት ካለባቸው የኢኮኖሚ እድገት ዉስንነት አንፃር  ለልማታችንም ሆነ ለዲሞክራሲየችን እድገት የሚያበረክቱት ትርጉም ያለው ተጽእኖ የላቸውም::  ሆኖም ግን ለአንዳንድ ጽንፈኛ ሀይሎች እንደመሸጋገሪያ በመሆን የሀገራችንን ሰላም ዲሞክራሲ እና መቻቻልን ሊያደፈርሱ ስለሚችሉ በዚህ ረገድ ልንከተው የሚገባው ፖሊሲ ችግሮቻችንን በንግግር በመፍታት የአደጋ ተጋላጭነታችንን መቀነስ ላይ የተመሰረ መሆን ይኖርበታል::