ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ
-------------------------------------------------------
የትምህርት ዝግጅት
- የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት፣
- ማስተርስ ዲግሪ (MA) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለም አቀፍ ግንኙነት፣
- ፒ.ኤች.ዲ (PHD) University of South Africa (UNISA) በፖሊሲ ሳይንስ አግኝተዋል፡፡
ዋና ዋና የስራ ልምዶች

- ከ1985-1991 ዓ.ም በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች፣
- ከ1992-1993 ዓ.ም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣
- ከ1994-2005 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣
- ከ2005-2009 ዓ.ም የትራንስፖርት ሚኒስትር በመሆን፣

- ከ2009 ዓ.ም ህዳር ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን፣

ከላይ በተዘረዘሩት ቦታዎች ባገለገሉባቸው ዘመናት የህዝቡንና የሀገሪቱን ሰላም የሚያስጠብቁ ስኬታማ ተግባራት በማከናወናቸው ዘመናዊና የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ሂደት ጠንካራ አመራር የሰጡ፤ በትራንስፖርት ሚኒስትርነታቸው ዘመን የመንገድ መሰረት ልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የከተማና ሀገር አቀፍ የባቡር መሰረተ ልማት የመንግስት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲሳኩ የበኩላቸውን ጉልህ የአመራር ድርሻ አበርክተዋል::