የአክሱምና የኢስላም ግዛቶች ግንኙነት የጥላቻ አልነበረም። ይህም የሆነው ነብዩ ሙሀመድ የእስልምና ሃማኖትን በሚሰብኩበት ወቅት እሳቸውን ሲከተሉ የነበሩ መዕምናን ላይ የመካ ቁረይሾች ስጋት ሲያሳድሩባቸው ባልደረቦቻቸውን ወደ አክሱም (ሀበሻ) ምድር ልከው በአክሱም ንጉሰ ከለላ በማግኘታቸው ነው። በእስልምና ሃይማኖት አሰተምህሮት መሰረት ነብዩ ሙሀመድየአረብ ኢስላሞች ወደ ሀበሻን ጅሃድ እንዳይዘምቱ አውጀዋል።
በዚህም ምክንያት የአክሱም መንግስት በአረቦች ዝንድ ልክ አንደ ሳሳኒያን ግዛት፣ እንደ ባይዛንታይን ግዛት ግዛትን እንደ ቻይና ግዛት ጥልቅ ቦታ ሰጥተውት ኑረዋል።የኋላ ኋላ እየቀነሰ ቢሄድም በቀይ ባህር ወደቦች መካከል ከአረቦች ጋር የንግድ ልውውት ቀጥሎ ነበር። የአክሱም መንግስት የገቢ ማስገኛዎቹንና ለሃይሉ ወሳኝ የነበሩትን ደቡብ መእራብ አረብን፣ የቀይ ባህር ወደቦችንና የንግድ ቦታዎችን እያጣ መጣ። በኋላም ቀስ በቀስ ወሳኝ ከሆኑ የግዛቱ ቦታዎች በማፈግፈግ የግዛቱን አቅጣጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በማድረግ ወደ አገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ማስፋፋት ጀመረ። በመጨረሻ አካባቢም አክሱም የንጊሶች ንግስና ዘውድ መጫኛና የሃይማኖታዊ ማዕከል ቦታዎች ብቻ ሁና ቀጥላለች።
ደቡባዊ ትግራይ አገው ኣካቢ የሚገኙት ላስታ፣ ዋግና አንጎት እንዲሁም የኣማራ አካባቢዎች ላይ በአክሱም ሃማኖታዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ትውፊቶች ላይ ተጽዕኖ ፈጥረዋል። በሌላ በኩል የሴም ቋንቋዎች፣ የአክሱም እደ ጥበብና ባህላዊ ትውፊቶች የክርስትና ሃይማኖት ወደ ሀገሪቱ ደቡባዊ አቅጣጫ እንዲስፋፋ በማድረግ እረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
በአስረኛው ክ/ዘመን የዛግዌ ክርሰቲያናዊ ስረወ መንግሰት ተመሰረተ። የዛግዌ ስረወ መንግስት ልክ እንደ አክሱም ስረወ ምንግስት ሁሉ አብዘናውን የደቡባዊ ኤርትራ ደጋማ ቦታዎችን፣ ሸዋን፣ የአዶሊስ የወደብ ዳርቻንና በሶማሌ ላንድ የሚገኙትን ደቡባዊ ዘይላ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል። ነገር ግን የቀይ ባህር የንግድ ማዕከል በአረብ ከሌፌት ስር ሁኖ መቀጠል ችላል።
የዛግዌ ስረወ ምንግስት የት እንደተናሳና መች እንደጀመረ የሚያመለክት ግልጽ ሆነ መረጃ አልተገኘም። ነገር ግን በ 10 ኛው ክ/ዘመን መቀመጫ ማዕከሉን ሮሃ ወይም አዳፋ አድርጎ ነበር ተብሎ ይገመታል። ኣካቢውም ላሊበላ ተብሎ ይጠራል። ላሊበላ ስያሜውን ያገኘው 12 ውቅር አብተ ክርስቲያናትን ሰርቷል ተብሎ ከሚገመተው የዛግዌ ስረወ መንግስት ንጉስና የሃይማኖት መሪ ነበር።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲናት በጣም አስደናቂና ለእይታ ማራኪ ናቸው። አብያተ ክርስቲያናቱ በዩኔስኮ (UNESCO) በአለም ቅርስነት ተመዝግበው ይገኛሉ። የመካከለኛው ዘመን የአውሮጳ ጽሐፊ ፓሪስተር ጆን ንጉሰ ላሊበላ ቅድሰት ምድር እየሩሳሌምን በማሰመለስ ስራ ላይ የመስቀል ጦረኞችን ሊረዳ ይችላል ተብሎ የሚጠበቅ ታላቅ የክርስቲያን መሪ አንደነበር ገልጿል።
በኋላም በ1270CE (Christian era) የአማራ መሳፍንት የሆኑት ዩኩኖ አምለክ የዛግዌን ሰረወ መንግስት መንግስት በማስወገድና ዘሩንም ከአክሱም መሪዎች ጀምሮ እስከ የእስራኤሉ ንጉስ ሰለሞን መሆኑን በማወጅ ራሱን አጼ ብሎ ሾመ፡፡ በዛን ዘመን የአፄ ዩክኖ አምላክን ስልጣን የሚያጠናክር ክብረ ነገስት የሚባል መጽሐፍ (ህግ) ተፃፈ፡፡ መፅሐፍ የአክሱም መሪዎች ዝርያቸው ከንግሰት ሳባና ከንጉስ ሰለሞን ከተወለደው አፄ ሚኒሊክ መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዩኩና አምላክ መንገስ የሰላምናዊ አገዛዝን እንዳስመለሰ ይታመናል፡፡ የዘግዌ መሪዎችም ከንጉስ ሰለሞን ዘር ስላልመጡ ስልጣን አይገባቸውም ብሎ ያምናል ዩኩኖ አምላክ፡፡
የሸዋ አማራ ስረወ መንግስት (ከ13 እስከ 16ተኛው ክ/ዘመን) የመካከለኛው ዘመን የኢትዬጵያን ስልጣኔ ይወክላል፡፡ በዚህ ዘመን የክርስትና ሀይማኖች በአገሪቱ የተስፋፋበት፣ የእደ-ጥበብ ስልጣኔ ውጤቶች ያበቡትና ትግራይ ውስጥ ብዙ ቤተክርስቲያናት ከአለት የተገነቡት ዘመን ነበር፡፡
ኋላ ኋላ የመጀመሪያው የሸዋ አማራ ግዛት አስተዳደር ከደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተነሱት ሀይለኛ የሙስሊም ስልጣኔዎች ፈተኑት፡፡ ከነዚህ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ሰሜን ምስራቅ ሸዋን የተቆጣጠረው የኢፋት ሱልጣኔትና ሀረርን ዋነኛ መቀመጫውን ያደረገው የአደል ሱልጣኔ ናቸው፡፡ በኋላም የአዳል ሱልጣኔት ቀይ ባህርንና ወደ እስልምና የገቡትን በአገሪቱ ምስራቅ አካባቢ የሚገኙትን አፋርና ሱማሌን በግዛቱ ስር አደረገ፡፡ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙት ሌሎች ሥልጣኔዎች በክርስቲያን ግዛት አስተዳደር ግብር እየገበሩ የሚኖሩት የሀድያ፣ የባሌ የዳወሮ፣ የፈታጋር፣ በምዕራብ አቅጣጫ የዳሞት ስልጣኔዎችና ግዛቶች ናቸው። በ15ኛው ክ/ዘመን በክርስቲያን ግዛቶችና በአደል ሱልጣኔዎች መካከል የመናቆርና የጠብ ሁኔታ ተጀመረ። ነገር ግን በ16ኛው ክፍለ ዘመን የግዛቱን ማዕከል ሐረር ያደረገውና በኋላም 1520 ውጤታማ የጦር መሪ የሆነው ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል ገአዚ በቅጽል ስሙ ግራኝ አህመድ ተፈጠረ፡፡ ኢማም አህመድ (አህመድ ግራኝ) የክርስቲያን ግዛት ሀይልን ለመስበር ውጤታማ የተባለለትን ጃሀድ አውጆ፣ በኋላም በ1529 ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጣሪ፡፡ ሰራዊቱም በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በመካከለኛው የኢትዮጵያ ዘመን የነበሩትንና የስልጣኔ መገለጫ የሆኑትን ህንፃዎች፣ ንዋየ ቅዱሳኖች፣ ባህላዊ ትውፊቶችና ቅርጻ ቅርጾች አውድሟል ተብሎ ይገመታል፡፡ በ1541 የፓርቱጋል ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መድረሳቸውን ተከትሎ የአዲሱ ስልጣኔት መሪ ኢማር አህመድ ከኦቶማን ቱርክ ወታደራዊ እርዳታ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን የፓርቹጋል ወታደሮች ቀድመው ደርሰው የገላውድዮስን ሀይል በመርዳት በ1543 በጣና ሀይቅ አካባቢ ኢማር አህመድ ተገደለ፡፡ የኣደል ስልጣኔትም ወደቀ፡፡ ነገር ግን የፓርቹጋሎች ዋነኛ ተልዕኮ የነበረው በህንድ ውቅጣኖስ የንግድ ማዕከሎች ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማጠናከር ነበር፡፡ ፓርቹጋሎች ኢትዬጵያ ውስጥ ከገቡ በኋላ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት እምነት ወደ ሮማን ካቶልክ እምነት እንዲለወጡ የመስበክ ስራ ጀመሩ፡፡ ይህ ተግባራቸው ግን በአገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ደረጃ የደረሰ ግጭት አስከትለ፡፡ ጦርነቱም እስከ 1632 ቀጥሎ ነበር፡፡ የነበረው ግጭት ከደቡባዊ ኢትዮጵያ አቅጣጫ በኩል ለተከሰተው የኦሮሞ አርብቶ አደሮች መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ከገናሌ ወንዝ በመነሳት ወደ ሰሜናዊ ባሌ እና ፍታጋር ላደረጉት መስፋፋት አጋዥ ካደጉት ምክንያቶች መካከል 1 በ1520 የተፈጠረው የክርስቲያን ግዛት መሪዎችና የአደል ሱልጣኔት መሪዎች ጦርነት እና የሲዳማ ኪንግደም መውደቅ ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡ መጀመሪያ አካባቢ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ዘመቻቸው ለዘረፋ የነበረ ቢሆንም የተቀናቃኞቻቸውን ድክመት ከተመለከቱ በኋላ በመጫላ ጋዳ ጊዜ (1554-1562) በአረፉባቸው አካባቢዎች መስፈር ጀመሩ፡፡
Pages: 1  2  3  4