ኢትዮጵያ  በአድዋ የተቀዳችው አንጸባረቂ ድል በአፍሪካ ብቸኛ ነፃ ሀገር ሆና ተለይታ እንድታተውቅ መሰረት የጣለ ታሪካዊ ሁነት ነው ለማለት ይቻላል። በተለይ በአድዋ ድል ላይ የተገኘው አስደናቂ ድል በዘመኑ ኃያላን የነበሩትን እንግሊዝ ና ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር አለም አቀፍ ስምምነት በመፈረም የኢትዮጵያን የነጻ ሀገርነት ህልውና እውቅና እንዲሠጡ አስገድዷቸዋል። ከነዚህ ሀገራት ባለፈም ድሉ ኢትዮጵያ ከቀረው አለም ጋርም ግንኙነት እንድትመሰርት እድል የፈጠረ በመሆኑ በቀጠሉት አመታት ከበርካታ አገሮች ጋር ግንኙነት ሊፈጠር ችሏል። የበርካታ ሀገራት ሚሲዮኖች ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ከጣሊያን፣ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ሩሲያ ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በዚሁ ግዜ ዉስጥ ተመስርቷል። ሮበርት ሰኪነር የተባሉ በፈረንሳይ ማርሴ ከተማ የአሜሪካ ቆንስላም በ1903 ኢትዮጵያን ለ9 ቀናት ከጎበኙ በኃላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ግንኙነትን የሚቆጣጠር ስምምነት ተፈርሟል።

አጼ ኃይለስላሴ መጀመሪያ በአልጋወራሽነት (1916) በኃላም በ1923 በንጉስነት ዙፋኑን ሲረከቡ ሀገሪቱን  ወደ ዘመናዊነት የሚወስዱ ጠንካራ ስራዎች መጀመራቸው ዲፐሎማሲ በሀገሪቱ ታሪክ ዉስጥ ማእከላዊ ስፍራን እየያዘ እንዲመጣ አስችሏል። በዚህም ምክንያት በርካታ የዉጭ ሃገራት ሚሲዮኖች ሲከፈቱ በኣንጻሩ ኢትዮጵያም ተወካዮቾን በተለያያ ሀገራት ልካለች። በዚህ ጊዜ ዉስጥም ኢትዮጵያ  በምእራቡ አለም የስልጣኔ ጎዳና ትልቅ እርምጃ የተራመደችበት እና ምእራባዊ የአኗኗር ዘይቤ መለመድ የጀመረበት ነው ለማለት ይቻላል። የራስ ተፈሪ በዐለ ሲመትም በርካታ የዉጭ ዲፐሎማቶች የተገኙበት ታሪካዊ ሁነት ሆኖ አልፏል።

በአጼ ኃይለስላሴ የመጀመሪያ ዘመናት ከተከናወኑ  የዲፕሎማሲ ተግባራት ትልቀ ቦታ የሚሠጠው በ1923 የኢትዮጵያ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ መግባት ቢሆንም ንጉሱ በኢየሩሳሌም ፣በግብጽ፣ጣሊያን፣ቤልጅየም፣ሉግዘምቦርግ፣ ሰዊዘርላንድ፣ ሰዊድን፣ እንግሊዝ ያደረጉት ጉብኝት ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኘ ዲፕሎማሲያዊ ሁነት ነበር። ኢትዮጵያ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ መግባት የሃገሪቱን ነጻ መንግስትነት የበለጠ ለማረጋገጥ ያለመ ቢሆንም ሀገሪቱ በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲደርስባት ህብረቱ ሊታደጋት አልቻለም። በታሪካዊው ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ንግግራቸው አጼ ኃይለስላሴ " ወራሪ ቢገጥማት ኢትዮጵያን ለመርዳት ቃል የገቡት ሀምሳ ሁለቱ አባል ሃገራትን አሁን የምጠይቃቸው ለኢትዮጵያ ለመርዳት ምን ለማድረግ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነው? እንደ ኢትዮጽያ ላሉ ደካማ ሀገራት በጋራ ደህንነት( collective security) መርህ መሰረት ድጋፍ ለመስጠት ቃል የገባቹህ ሓያላን ሀገራት ጥቃቱ አይሏ የኢትዮጵያ እጣ ይደርሳቹህ ይሆናልና እኛንለመታደግ ምን ለማድረግ አስባቹኃል? የአለም መንግስታት ተወካዮች እፊታቹህ የተገኘሁት የአንድ ሀገር መሪ ሊወጣው ከሚገባው ሃላፊነት መራራውን ለመወጣት ነው ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ኢትዮጵያን ሊታደግ አለመቻል በጋራ ደህንነት( collective security) ታሪክ ላይ ጥቁር ጠባሳን ጥሎ ያለፈ ሁነት ሆኖ አልፏል።

ይሁን እንጂ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ታሪካዊ ስህተት ኢትዮጵያን በጋራ ደህንነት( collective security) መርህ ላይ ያላትን አቋም አልለወጠውም ይልቁኑም በተግባር እንዲተረጓም የበኩሏን ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። በዚሁ ጥረት መነሻነትም  ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ሲመሰረት መስራች አባል ከመሆኗም በላይ በመርሁ ተግባራዊነት ዙሪያ ከፍተኛ ግምት በሚሠጠው የሰላም ማስከበር ስራ ትልቅ ሚና ተጫውታለቸ።በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በኮሪያ፣ኮንኀ፣ በቅርብ ከተካኄዱ ደግሞ  በርዋንዳ፣ቡሪንዲ፣ላይቤሪያ፣ሱዳን የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልእኮዎች ላይ  በመሳተፍ ያሳየቸው ሚና በአርአያነት የሚጠቀስ ነው።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታን በተመለከተም ኢትዮጵያ በድርጅቱ መስራች ጉባኤ ላይ የተራራቀ አቋም የነባራቸውን የሞኖሮቪያ ና የካዛብላንካ ቡድኖች በማቀራራብ የአኅጉራዊው ተቐም ምስረታ እዉን እንዲሆን ትልቅ ሚና ተጫውታለች። የህብረቱ መቀመጫ ፣የተባባሩት መንግስታት የአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንዲሁም የሌሎች ታላላቅ አለምቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆንም የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መናኅሪያ ለመባል በቅታለች።

ለ17 አመታት በዘለቀው የወታደራዊው ጁንታ አገዛዝ ስርአቱ ይከተለው በነበረው ወደ ምስራቁ ጎራ ያደላ የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲ ምክንያት ኢትዮጵያ  ከበርካታ ሀገራት ጋር የነበራት ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። እንደ እ.ኤ.ኤ በ1991 የደርግ ስርአት መደምሰስን ተከትሎ በኢትዮጵያ አዲስ  ዴሞከራሲዊ ስርአት በመተከሉ በሃገሪቱ የዉጭ ግንኙነት አዲስ ምእራፍ ተከፍቷል። አዲሱ የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥለው ድህነት መሆኑን በመተንተን የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲው ስራው ዋና ጉዳይ የሀገር ዉስጡን የልማት ስራ ማገዝ መሆኑን ያሰረዳል። ለዚሁ አላማ መሳካትም በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነት፣ በሀገሮች የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባትን እንዲሁም ክልላዊ ዉህደትን እንደ መርህ ያስቀምጣል። ፖሊሲው ዋነኛ ግቡን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በማድረግ በተደረገው ርብርብም ሀገራችን ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ላላፉት 9 አመታት አስመዝግባለች። በፓለቲካዊ ዲፕሎማሲውም ረገድ ኢትዮጵያ ከበርካታ ሀገራት ጋር ስትራተጂካዊ አጋርነት ስትመሰረት በጥቅሉም ጎረቤት ሀገሮችን ጨምሮ ከበርካታ ሃገሮች ጋር መልካም ግንኙነትን አዳብራለች። ክልሉን በኢኮኖሚ አንድ ለማድረግ በሚደረገው ጥረትም ግንባር ቀደም በመሆን በመንገድ ፣በሀይል ማስተላለፊየዎች ፣ በባቡር መስመር ዝርጋታ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች'። በሳማሊያ በሱዳን የሰላም ጥረቶች ተጠቃሽ ሚና በመጫወት የክልሉ የሰላም ሻምፒን ለመባል በቅታለች። በ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአስተዳደር ዘመንን የአፍሪካ ድምፅ በመሆን የአካባቢ ጥበቃን በመሳሰሉ በተለያዩ አለምቀፍ ጉዳዮች አፍሪካን በመወከል የአህጉሪቱን ጥቅም ለማስከበር ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ስራ ተከናውኗል ።

Pages: 1  2