የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አጭር ታሪክ

የኢትዮጵያ ከከሶስት ሺህ አመት በላይ ያስቆጠረ የመንግስትነት ታሪክ ያላት ጥንታዊ ሀገር ናት። ሃገራችን ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና ኤዥያ መተላለፊያ(cross road) በመሆንዋ ምክንያት የዉጭ ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክዋ አካል ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ከውጭ ሃይሎች ጋር የነበሩ የንግድ ግንኙነቶች እንዲሁም ደም አፋሳሽ ግጭቶች በሃገራችን ታሪክ ዉስጥ ዉስጥ የዘለቁ ተጠቃሽ ሁነቶች ናቸው። በግርድፍ አነጋጋር የኢትዮጵያ ዘመናዊ የዲፐሎማሲ ታሪክ ጅማሮ ተብሎ የሚወሰደው ጊዜ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ቴዎድሮስ ከምእራባውያን ሀገራት የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር የጀመሩበት ወቅት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ አጼ ቴዎድሮስ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የነበራቸው ህልም ከብዙ ሃይሎች ጋር ያጋጫቸው ስለነበር ህልማቸውን እውን ለማድረግ ከምእራቡ አለም ዘመናዊ መሳሪያ እና ቴክኖሎጂን ወደ ሃገር ማስገባት እንደሚያስፈልግ በጽኑ ያምኑ ነበር። በጄኔራል ናፒየር በሚመራው እንግሊዝ ጦር ተሸንፈው ራሳቸውን እስካጠፉበት ጊዜ ድረስም የውጭ መልክተኞችን በእልፍኛቸው በመቀበል ሀገራቸውን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ይመክሩ ነበር።

በእርሳቸው ዙፋን የተተኩት አጼ ዮሃንስ IVም ቢሆኑ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጀመረውን ከምአራባውያን ሀገሮች ግንኙነት ገፍቶ የመሄድ ጠቃሚነት ጠንቅቀው በመገንዘብ በርከታ ግንኙነቶችኙን ያደርጉ ነበር። አጼ ዮሃንስ IV በሱዳን ከማህዲስቶች እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ ከጣሊያን የመስፋፋት እንቅስቃሴ ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ  ዉስጥ የነበሩ በመሆናቸውም በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ግንጘኙቶችን ያደርጉ ነበር፡ በተለይ በ Augustus Wylde (1883), Vice-Admiral Hewett 1884 እና Gerald Portal (1887) በተባሉ ሰዎች የተመሩ የእንግሊዝ ልኡካንን በመቀበል በማሃዲስቶች ስር የነበረውን የግብጻውያን የጦር ሰፈር ነጻ ስለሚወጣበት ሁኔታ፣ እንግሊዝ በቁጥጥርዋ ስር የነበረውን የምጽዋ ወደብ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል ስለመግባትዋ እንዲሁም በተመሳሳይ ምጽዋን ለኢጣሊያ ሰጣለሁ ስለማለቷ ጉዳይ መነጋገራቸው በወቅቱ ስለነበረው የዲፐሎማሲ እንቅስቃሴ በአብነትነት የሚጠቀስ ነው።

በአፄ ምኒሊክ ዘመን ኢትዮጵያ  የዘመናዊ ስልጣኔ  ጉዞን በስፋት የጀመረችበት ጊዜ በመሆኑ ከምእራባውያን ሀገራት ቴክኖሎጂ ፣ክህሎት እና ወረት  በማስፈለጉ ከዚሁ ጋር የሚተካካል ዲፕሎማሲ ማድረግን የግድ የሚል ሁኔታ ነበር ለማለት ያስደፍራል።በተለይም አፍሪካን የመቀራመት ጉባኤ ተብሎ የሚጠራው ጉባኤ በበርሊን ከተካሄደ በኃላ ኢትዮጵያ  ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና እንግሊዝ በአካባቢው እያደረጉ ከነበረው የመስፋፋት እንቅስቃሴ አንጸር እንደ ሀገር ህልውናዋን ጠብቃ ለመቆየት ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ተገዳ ነበር። በዚሁ ወቅትም ነበር ግብጾች በሱዳን ማሀዲስቶች እጅ አሳፋሪ ሽንፈት ስለደረሰባቸው የኤርትራን የባህር ዳርቻ አካባቢ ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ጣሊያን ምፅዋን በመቆጣጠር ወደ መሃል አገር የመስፋፋት እንቅስቃሴ ዉስጥ የገባቸው።አፄ ምኒሊክ በ1889 ወደ ስልጣን በመጡበት ጊዜ ጣሊያን ከመረብ ምላሽ ያለውን ግዛት የተቆጣጠረው የመሆኑ ጉዳይ ትልቀ ፈተና እንደሆነባቸው ታሪክ ያስታውሳል። በዘመኑ ከተካሄዱ የዲፕሎማሲ ሁነቶች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የዉጫሌ ስምምነት የተፈረመው በዚሁ አመት (በ1889) አጼ ዮሃንስ IV ከሞቱ ከጥቂት ጊዜያት በኃላ ነበር።። ስምምቱ በተፈረመበት ወቅት ሁለቱም ወገኖች በስምምነቱ አተረጓጓም ምክንያት ወደ ታላቅ ዉጊያ እናመራለን በለው ባይገምቱም Count Antonelli, የተባለው የጣሊያን ልኡክ ግን የስምምነቱ አንቀጽ 17 የአማርኛው ቅጂ አፄ ምኒሊክ ከዉጭ መንግስታት ጋር ለመገናጘኘት ሲፈልጉ በጣሊያንን መንግስት ለመገናኘት ይችላሉ ሲል በተቃራኒው የጣልያንኛው ቅጂ ግን ንጉሱ የዉጭ ግንኙነት ሊያደርጉ የሚችሉት በጣሊያን መንግሰት ብቻ ነው ስልሚል በሁለቱ ቅጂዎች መካካል የትርጉም መፋለስ እንዳለ ያውቅ ነበር። ይኸው የትርጉም ልዩነት አጼ ምኒሊክ ስምምነቱን በ1893 እንዲሽሩት ሲያስገድዳቸው በኃላም ሀገራችንን በኃይል ለመያዝ የቃጣው የኢጣሊያ ጦር በንጉሱ እየተመራ ከመላ ሀገራችንን የተመመውን ጦር እ.ኤ.አ 1896  አድዋ ላይ ገጥሞ  አሳፋሪ ሽንፈትን ተከናንቧል።

Pages: 1  2