የሰው ዘር መገኛ ኢትዮጵያ፡
የሰው ዘር አመጣጥ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ አብዛኛውን የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ትሸፍናለች። የቅሪተ አካል ምርምር ማስረጃዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ ከ Chororapithecus Abyssinicus ( 12-7 ሚሊዮን አመት በፊት የተገኘው ሰው መሳይ ጦጣ) ጀምሮ እስከ homo sapiens(ብልቱ ሰው) እየተባለ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን ትሸፍናለች። ይህም ማለት በአፋር ክልል ሆርቶ አካባቢ ከ 160,000 እድሜ እስካለው የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት ማለት ነው።
በቅርቡ ከተገኙ ግኝቶች ደግሞ 4.4 ሚሊዮን አመት ያለው Ardipithecus kadaba እና ከ 3.3 ሚሊዮን አመት በፊት ኑራለች ተብሎ የሚገመተው የተሟላ ሰውነት ያላት ሰላም ይገኙባታል። በቅሪጸ አካል ግኝት በጣም ታዋቂ ሆነችውና ከተሟላ የሰውነት አካላ ጋር የተገኘችው ሉሲ በሳየንሳዊ አጠራሯ "Australopithecus Afarensis" ወይም ድንቅነሽ የሚል መጠሪያ የተሰጣት ከ3.2 ሚሊዮን አመት በፊት ጥኖር የነበረችውና በጊዜው በሁለት እግሮቿ መንቀሳቀስ የቻለች የሶስት ጫማ ርዝመት ያላት ናት።
ሉሲ የተገኘችው በአፋር ክልል ሃዳር በሚባል አካባቢ ነው። በአሁኑ ወቅት የሉሲን ምስል የያዘው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም ውስጥ ለሁሉም ጎብኚዎች ክፍት ሁኖ ይገኛል። በአጠቃላይ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ የሚጀምረው ከ Australopithecus ሲሆን በሂደትም ወደ ተቀየረ፡፡ Genus homo ሶስት የለውጥ ሂደቶች አሉት በቅደም ተከተልም እንዲህ እናስቀምጣቸዋለን።
1, Homo habilse (2.4-1.8 ሚሊዮን አመት) 2, homo erectus ( ከ 1.4-1 ሚሊዮን አመት) 3, homo sapiens (ከ200,000 አመት በፊት)
የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1000 BC እስከ 1991 EC
ኢትዮጵያ በተደራጀ ሁኔታ ታሪኳ የሚጀምረው ከመጀመሪያው ሚሊኒየም ቅድመ ልደተ ክርሰቶስ ነው። በድወሮው ዘመን የግብጽ ፎርኦኖች ከፑንት ላንድ ጋር የንግድ ልውውጥ ሲያደርጉ ነበር። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት ፑንት ላንድ የሚባለው ኣካባቢ አሁኑ የኤርትራ ዳርቻዎች ወይም ሶማሌ ላንድ ነው።
የደአማት ስረወ መንግስት በ8ተኛው መቶ ክ/ዘመን መቀመጫውን የሐ የሚባል ቦታ አድርጎ እነደነበር ይታመናል ። ሁኖም ግን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መንግስትና የተማላ መረጃ የሚገኝለት ስረወ መንግስት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ትግራይ ክልል ውስጥ የተመሰረተው አክሱም ስረወ መንግስት ነው።
የአክሱም ስረወ መንግስት ለመውደቅ ከመዳረጉ የተወሰኑ መቶ አመታት በፊት ስረወ መንግስቱ ከ አራተኛው ክ/ዘመን ክርስትና ሃይማኖት መምጣት ጀምሮ የተመሰረተና እንደ ኢሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 800 CE ተጽእኖ ፈጣሪ ሆነ ሃያል መንግስት ነበር። የአክሱም ስረወ መንግስት መቀጠል የቻለው ከ 4ተኛው መቶ ክ/ዘመን እስከ 6ተኛው መቶ ክ/ዘመን ነበር።
ማዕከሎቹን አክሱምና አንጎት አድርጎ ይንቀሳቀስ የነበረው የአክሱም ስረወ መንግስት ደቡባዊ ኤርትራ ፣ ትግራይ እና በኣሁኑ ጊዜ በአማራ ክልላዊ መንግስት የሚገኙት ላስታና አንጎት ዋነኛ የግዛት አካባቢዎች ነበሩ። እንደ የሃ አይነት ቀደምት ማዕከሎችም ለአክሱም ስልታኔ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የአክሱም ስረወ መንግስት መሪዎች ሰዋክን (በአሁኑ ጊዜ ሰሜናዊ ሱዳን አካባቢ የሚገኝ) ቀይ ባህርና በርበራን ( በአሁኑ ጊዜ ደቡባዊ ሶማሌ ላንድ) የሚገኙ ቦታዎችን በቁጥጥር ስራቸው አድርገዋል።
በተጨማሪም የአክሱም ነገስትታት በ 4ተኛው ክ/ዘመን በዘመናዊት ሱዳን በአባይ ሸለቆ ላይ የበላይነታቸውን በመያዝ የሜርዌ ግዛት ላይ ጥቃት በመክፈት ግዛቷን አውድመዋታል። በአረቦች በኩል የሚገኙትን የቀይ ባህር አካባቢዎችን፣ የቀይ ባህር ዳርቻዎችንና ዘመናዊት የመንን በግዛታቸው ስር አስገብተዋል። የአክሱም መሪዎች በአራተኛው ክ/ዘመን ወደ ክርስትና ሀይማኖትን ተቀብለዋል። በሰበተኛው ክ/ዘመን በኣረብ ባህረ ሰላቴ የተነሳው የእስልምና ሃይማኖት ለአክሱም ስረወ መንግስት መንኮታኮት ትልቅ ሚና ነበረው። ነብዩ ሙሀመድ በሞቱበት ወቅት (.A.D. 632) የኣብዛኛው የአረብ ባህረ ሰላጤና የቀይ ባህር ዳርቻዎች በእስልምና ሃይማኖት ስር ሆነዋል። በፍጥነት እየተስፋፋ የሄደው የእስልምና ሃይማኖት የባይዛንታይን ግዛትንና የሳሳኒያን ግዛት በኢስላማዊ አገዛዝ ስር እንዲወድቁ አድርጓል።

Pages: 1  2  3  4