የአውሮፓ ሕብረት አገራት ሊኖረን የሚገባው ግንኙነት

ይህ አካባቢ ለኢኮኖሚ እድገታችን ወሳኝ የሆነ ቦታ ነው። በመሆኑም አካባቢው ላይ ልንከተለው የሚገባ ፖሊሲ  ለምርቶቻችን ገበያ በማፈላለግ፣ ለልማታችን ብድር እና እርዳታ እንዲሁም የውጭ  ኢንቨስትመንት ከመሳብ አንፃር የተቃኘ መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም የአውሮፓ አገራት በዓለም ላይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን ካላቸው ቁርጠኝነት አንፃር ለዲሞክራሲ ግንባታችን ከፍተኛ እገዛ ሊያበረክት ይችላል፡፡  በመሆኑም እስካሁን ያለብንን አህጉሩ የሚያበረክተውን እድል አሟጦ የመጠቀም ችግር፤ በተጨማሪም በአህጉሩ ስላሀገራችን ያለውን የገጽታ ችግር በመቅረፍ ተጠቃሚነታችንን ከፍ የሚያደርግ ፖሊሲ መከተል ይኖርብናል ፡፡