4.     እንዲረጋገጡ የሚቀርቡ ሠነዶች የሚኖራቸው የአገልግሎት የጊዜ ገደብ

4.1.     ጠቅልለው ወደ ሀገራቸው  ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀረጥ ከፍለው እንዲያስገቡ ከሚሲዮኖቻችን የተጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ከተጻፈ ቀን ጀምሮ አንድ ዓመት ካለፈው አይረጋገጥም።

4.2.     የትምህርት፣ የልደትና የሞት ማስረጃ በሰነዱ ላይ ያለው የማህተም፣ የኃላፊ ፊርማና ቲተር ናሙና በመ/ቤቱ   የፊርማ ናሙና ዳታ ቤዝ እስካለ ድረስ ምንጊዜም ይረጋገጣል።

4.3.     ከላይ በንዑስ አንቀጽ 4.1 እና 4.2  ከተገለጸው ውጪ ሌሎች ሠነዶችን በሚመለከት በመ/ቤቱ የማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት  የሚቀርቡት ለመጨረሻ ጊዜ ሥልጣን ካለው አካል ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ 2 ዓመት ያላለፋቸው ይረጋገጣሉ።

4.4.      ከላይ በንዑስ አንቀጽ 4.1፣4.2 እና 4.3 የተገለጹት እንደተጠበቀ ሆኖ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ሠነዶች       አይረጋገጡም።

4.5.     ከሚመለከተው አካል ተፈርሞ ወይም ተረጋግጦ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የ2 ዓምት ጊዜ ያለፈበት ሠነድ በሚመለከተው አካል ታድሶ ወይም ተገቢውን ቅድመ ሁኔታ ያሟላ ሌላ አዲስና ተመሳሳይ ሠነድ ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

4.6.     ቀደም ሲል በመ/ቤቱ የተረጋገጡና የእድሳት አገልግሎት የሚጠየቅባቸዉ ሠነዶች አገልግሎት ሊያገኙ የሚችሉት በመ/ቤቱ ከተረጋገጡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡

Anchor

ተ.ቁ.

የሠነድ አይነት

የአገልግሎት ክፍያ በብር

ለኢትዮጵያውያንና የአትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ላለቸዉ

ለውጭ ዜጋ

1.     

የመታወቂያና ፓስፖርት ኮፒ

150

300

2.     

የትምህርት ምስክር ወረቀት

150

300

3.     

መንጃ ፍቃድ

150

300

4.     

የጋብቻ ምስክር ወረቀት

150

300

5.     

ያላገባ  ምስክር ወረቀት

150

300

6.     

የፍቺ ምስክር ወረቀት

150

300

7.     

ከወንጀል ነፃ ምስክር ወረቀት

150

300

8.     

የልደት ምስክር ወረቀት

150

300

9.     

የሞት ምስክር ወረቀት

150

300

10.     

አሻራ ምስክር ወረቀት

150

300

11.     

የሐኪም ምስክር ወረቀት

150

300

12.     

የስራ ውል

162

324

13.     

የስራ ልምድ

162

324

14.     

የፍርድ ውሳኔ

162

324

15.     

ቃለ ጉባኤ

162

324

16.     

ስምምነትና መተዳደሪያ ደንብ

162

324

17.     

ቃለ መሃላ

162

324

18.     

ኑዛዜ

162

324

19.     

የይዞታ ማረጋገጫ

162

324

20.     

የትብብርና የድጋፍ ደብዳቤ

162

324

21.     

የሙያ ፈቃድና ብቃት ማረጋገጫ

162

324

22.     

ለሚመለከተው በሚል የተዘጋጁ ሠነዶች

162

324

23.     

ውክልና

162

324

24.     

የጉዲፈቻ ውል

162

324

25.     

የንግድ ሠነዶች

162

324

26.     

የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ

162

324

27.     

የጡረታ መታወቂያ ኮፒ

162

324

28.     

የእድሳትና የማወራረስ አገልግሎት

ነፃ

ነፃ

ለበለጠ መረጃ

(     0115510043/0115510076

 

*     393

Pages: 1  2  3  4  5