1.1.11.     የኢንቨስትመንት ፈቃድና ሌሎች ኢንቨስትመንት ነክ ሠነዶች

v     ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር የሚመነጩ፣ በከተማ መስተዳድሩ ኢንቨስትመንት ቢሮ፣

v     ከብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ሠነዶች፣ በየክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ወይም በክልሉ መንግሥት ይህንኑ ተግባር እንዲያስፈጽም ስልጣን በተሰጠው የአስፈፃሚ አካል ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     በፌዴራል ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የተሰጡ፣ በኤጀንሲው የሚመለከተው ኃላፊ ተፈርመው ሲቀርቡ በቀጥታ ይስተናገዳሉ፡፡

1.1.12.     የጉዲፈቻ ሠነዶች

v     በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ተሰጥተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዋና ሪጅስትራር ጽ/ቤት ተረጋግጠው መቅረብ አለባቸው፡፡

v     ከክልሎች የተሰጡ የጉዲፈቻ ሰነዶች በክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተረጋግጠው መቅረብ አለባቸው፡፡

1.1.13.     የጡረታ መታወቂያ  ኮፒ

v     የጡረታ መታወቂያ ኮፒ በማህበራዊ ዋስትናና ጡረታ ኤጀንሲ መረጋገጥ ይኖርበታል።

1.1.14.     "ለሚመለከተው ሁሉ" በሚል የተዘጋጁ ልዩ ልዩ ሠነዶች

v     ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካላት የሚመነጩ፣ አመንጭው መ/ቤት ተጠሪ ለሆነው በመስተዳድሩ ቢሮ፣

v     ከአዲስ አበባ ከተማ የሚመነጩ፣አመንጭው መ/ቤት ተጠሪ ለሆነው በክፍለ ከተሞቹ ጽ/ቤቶች ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣

v     በብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ሥር ካሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚሰጡ፣ አመንጭው መ/ቤት ተጠሪ ለሆነው በክልሉ ቢሮ፣

v     ከፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች የሚሰጡ፣ ከየመ/ቤቶቹ በሚመለከተው ባለስልጣን፣

                 ተረጋግጠው መቅረብ አለባቸው።

1.1.15.     ሌሎች አግባብነት ያላቸውና ከዚህ በላይ ያልተገለጹ ሠነዶች

v     ከዚህ በላይ ከተገለጹት ውጭ ማንኛውም ሠነድ በመ/ቤቱ ሊረጋገጥ የሚችለው አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሰጠ ወይም ሠነዱ ከመነጨበት አካል ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው ቢሮ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

v     መንግስታዊ ካልሆኑ የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ ሠነዶች ለተቋሙ ዕውቅና ወይም ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጠው የመንግስት መ/ቤት ተረጋግጦ መቅረብ አለባቸው።

1.2.     ከኢትዮጵያ ውጭ የሚመነጩ ሠነዶች

v     መነሻቸው ከኢትዮጵያ ውጭ የሆኑ ሠነዶች በመነጩበት አገር በሚገኝ የኢትዮጵያ ሚሲዮን ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝና ሠነዶቹ የመነጩበትን አገር በሚወክል ሚሲዮን ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

v     ሠነዱ የሚመነጭበትን አገር የሚወክል ሚሲዮን ከሌለ ሀገሪቱን የሚከታተል በኢትዮጵያ ሚሲዮን ወይም ሀገራችንን የሚከታተል የሀገሪቱ ሚሲዮን ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል።

2.     እድሳት ወይም በድጋሚ ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው ሠነዶች

2.1.     ቀደም ሲል በሚኒስቴር መ/ቤቱ ተረጋግጠው የነበሩ ሠነዶችን ለማሳደስ ጥያቄ ሲቀርብ፣

v     ቀደም ብሎ  የተረጋገጠው ሠነድ ዋናው (ኦሪጂናሉ) መቅረብ ይኖርበታል።

v     በመ/ቤቱ የተረጋገጡ ሠነዶች በሚመዘገቡ ፋይል ውስጥ ተመዝግቦ መገኘት ይኖርበታል።

v     ተመዝግቦ ያልተገኘ ሠነድ እድሳት ሊያገኝ አይችልም።

v     ሠነዱ ተመዝግቦ መገኘቱ ሲረጋገጥ በዋናው (ኦሪጂናሉ) ላይ "ተመዝግቧል" ይም ("Registered ") የሚል  ማህተም ተደርጎበት የማረጋገጫ አገልግሎት ይሰጠዋል።

2.2.     ከዚህ ቀደም በሚኒስቴር መ/ቤቱ ተረጋግጠው የነበሩ ሠነዶች በይዘታቸው ስህተት ሲያጋጥምና በሌላ ተለዋጭ አዲስ    ተመሳሳይ ሠነድ ተተክተው እንዲወራረሱ ወይም በድጋሚ ለማረጋገጫ በሚቀርቡበት ጊዜ፣

v     ቀደም ብሎ የተረጋገጠው ዋናው(ኦሪጂናል) ሠነድ ከአዲሱ ወይም ከተለዋጩ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።

v     ቀደም ብሎ የተረጋገጠው ሠነድ በመ/ቤቱ የተረጋገጡ ሠነዶች በሚመዘገቡበት ፋይል ተመዝግቦ መገኘት ይኖርበታል።

v     በመ/ቤቱ ፋይል ተመዝግቦ መገኘቱ ሲረጋገጥ ቀደም ብሎ በተረጋገጠው ዋናው ሠነድ ላይ የሚገኘው የመ/ቤቱ የማረጋገጫ ፊርማና ማህተሞች ተሰርዘው ተለዋጩ ሠነድ በተሰረዘው ሠነድ ላይ በነበረው ተመሳሳይ ቀንና የመዝገብ ቁጥር ይረጋገጣል።

v     በሠነዱ መሠረታዊ ይዘትና ዓይነት እንዲሁም ሠነዱን አረጋግጦ ከሰጠው አካል ጋር ተመሳሳይነት የሌላቸው ሠነዶች አይወራረሱም።

3.     የሠነድ ማረጋገጫ አገልግሎትን በማስመልከት በደብዳቤ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ስለማስተናገድ 

3.1.     በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተረጋገጡ ስለመሆናቸው አጠራጣሪ የሆኑ ሠነዶችን በሚመለከት ተጣርቶ ምላሽ  እንዲሰጣቸው ከተለያዩ አካላት ጥያቄዎች ሲቀርቡ፣

v     የሚጣራው ሠነዱ ሙሉ ፎቶ ኮፒ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።

v     የሚጣራውን ሠነድ ኮፒ በሚኒስቴሩ ከሚገኝ የሠነድ ማረጋገጫ መዛግብትና ከአገልግሎቱ የአሰራር መመሪያ ጋር በማገናዘብና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የሚገኘውን ውጤት መሠረት ያደረገ የመልስ ደብዳቤ ተዘጋጅቶ ለጠያቂው አካል እንዲደርስ ይደረጋል።

v     ጥያቄው የሠነዶችን ይዘት የሚመለከትና ከሚኒስቴሩ በቀጥታ ምላሽ ሊሰጠው የማይቻል ሲሆን የሚመለከተው አካል በደብዳቤ በመጠየቅ የሚገኘውን ምላሽ መሠረት በማድረግ ለጠያቂው አካል በደብዳቤ እንዲገለጽለት ይደረጋል።

3.2.     በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ሚሲዮኖች፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች የፊርማና የማህተም ናሙናዎቻቸው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣንና ለሚመለከታቸው ሌሎች የመንግስት ተቋማት እንዲተላለፍላቸው ሲጠይቁ፣

v     እንዲላክላቸው የሚፈልጉትን የናሙና ሠነድ ሦስት ገጽ(አንድ ኦሪጂናልና 2 ኮፒ) ከሸኚ ደብዳቤ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

v     እንዲተላለፍላቸው ያቀረቡትን የናሙና ሠነድ በመ/ቤቱ የናሙና ማስተላለፊያ ሸኚ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ ለተፈለገው የመንግስት ተቋም እንዲተላለፍ ይደረጋል።

Pages: 1  2  3  4  5