1.1.4.     የመንጃ ፍቃድ

v     በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞች መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የተሰጡ በቀጥታ ይስተናገዳሉ፡፡

v     ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር የተሰጡ በከተማ መስተዳድሩ  መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     ከብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የተሰጡ ከሆኑ በክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.5.     የአሻራ(ከወንጀል ነፃ)ማስረጃ

v     ይህ ማስረጃ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀልና የፎረንሲክ ምርመራ ዋና መምሪያ የተሰጠ መሆን አለበት፡፡

1.1.6.     የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ

v     የኢትዮጵያ ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

1.1.7.     የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ ብይን፣ ትዕዛዝ የሚመለከቱ ሠነዶች

v     ከድሬዳዋና አዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች የተሰጡ፣ በየፍ/ቤቶች ሪጂስትራር ጽ/ቤቶች፣

v     በብሔራዊ ክልልዊ መንግሥታት በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ ፍ/ቤቶች የተሰጡ፣ በየክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ሪጂስትራር ጽ/ቤቶች ወይም በክልሉ መንግሥት ይህንኑ ተግባር እንዲያስፈፅም ስልጣን በተሰጠው የአስፈፃሚ አካል፣

v     ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛ ደረጃና ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የተሰጡ ሠነዶች በፍ/ቤቶቹ ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት፣

v     ከክልሎች/ከተማ መስተዳድሮች ሸሪዓ ፍ/ቤቶች  የተሰጡ ሰነዶች በየክልሎቹ/ከተማ መስተዳድሮቹ ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ/ቤቶች፣

             ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.8.     የውክልና፣ የዲክለራሲዮንና የቃለ-መኃላ  ሠነዶች

v     ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የሚመነጩ በከተማ መስተዳድሮቹ ደረጃ በተቋቋሙ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤቶች ወይም ስልጣን በተሠጣቸው አካላት ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     ከብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የመነጩ በክልሉ ፍትሕ ቢሮ ወይም ሥልጣን በተሠጣቸው አካላት ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.9.     የሕጋዊ ሠነዶች ትርጉም

v     የአንድን ሰነድ ትርጉም ለማረጋገጥ ሲፈለግ በቅድሚያ ዋናውን ሰነድ በዚህ መመሪያ እንደየሰነዱ ዓይነት የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

v     ትርጉሙ እንዲረጋገጥ የሚፈለገው ሰነድ ከዋናው ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡

v     የትርጉም ሠነዶችን የመተርጐም ሕጋዊ ፈቃድ ባለቸው የትርጉም ድርጅቶች የተተረጐሙ  መሆን አለባቸው፡፡

v     ከድሬዳዋና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድሮች የሚመነጩ ሠነዶች ለትርጉማቸው ትክክለኛነት በከተማ አስተዳደሮቹ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤቶች መረጋገጥ አለባቸው፡፡

v     ከብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት የተላያዩ አከባቢዎች የሚመነጩ ሠነዶች በየክልሉ ደረጃ ባሉት ፍትሕ ቢሮዎች ተረጋግጠው መቅረብ አለባቸው፡፡

1.1.10.     የንግድ ፈቃድና ንግድ ነክ ሠነዶች

v     ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተሰጡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚመለከተው ኃላፊ፣

v     ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር የተሰጡ የንግድ ፈቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሠነዶች በመስተዳድሩ የንግድ ቢሮ፣

v     ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የሚመነጩ፣ በየክፍለ ከተሞቹ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ወይም በአስተዳደሩ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ፣

v     ከብሔራዊ ክልልዊ መንግሥታት የተለያዩ ቦታዎች የሚሠጡ፣ በክልሎቹ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ወይም በክልሉ መንግሥት ይህንኑ ተግባር እንዲያስፈጽም ስልጣን  በተሰጠው አስፈፃሚ አካል፣

v     የወጪ ምርቶችን የሚመለከቱ የcertificate of origin ሠነዶች፣ በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት፣ በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትና በክልል በሚገኙ ንግድ ምክር ቤቶች፣

v     ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች የጤና ምርመራ፣ የኳራንቲን እና የመሰሳሉትን የሚመለከቱ ሰነዶች እንደአስፈላጊነቱ በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ በግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣

ተረጋግጠው መቅረብ አለባቸው፡፡

Pages: 1  2  3  4  5