1.1.2.2.     የ10ኛ /12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምስክር ወረቀት

v     የ10ኛ /12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምስክር ወረቀቶች በአገር አቀፍ የፈተናዎች ምዘና ኤጀንሲ ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.2.3.     እስከ ደረጃ IV / ዲፕሎማ ያሉት የትምህርት ማስረጃዎች

v     ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የተሰጡ፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ፣

v     ከአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የተሰጡ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ፣

v     ከክልል መስተዳድሮች በመንግስትና በግል የትምህርት ተቋማት የተሰጡ፣ በየክልሉ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ፣

                 ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.2.4.     ከግል የትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ዲግሪና ከዚያ በላይ ለሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች

v     ከግል የትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ዲግሪና ከዚያ በላይ ለሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች በትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.2.5.     ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች

v     ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች በዩኒቨርሲቲው ሪጂስትራር ጽ/ቤት መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣

1.1.3.     ከጤና ተቋማት የሚሰጡ የሕክምና ማስረጃዎችና ሌሎች ሠነዶች

v     በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙ የጤና ተቋማት የተሰጡ፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣

v     በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ከሚገኙት የጤና ተቋማት የተሰጡ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣

v     በብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ሥር በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት  የተሰጡ በየክልሉ ጤና ቢሮዎች ወይም በክልሉ መንግስት ይህንኑ ተግባር እንዲያስፈጽም ሥልጣን በተሰጠው የአስፈፃሚ አካል ፣

v     በከተማ አስተዳደር ወይም በክልሎች ሥልጣን ሥር ካልሆኑት የጤና ተቋማት የተሰጡ ማስረጃዎች በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣

ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5