የማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የሚቀርቡ ሠነዶች መሟላት ስለሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች

1.1.     ከኢትዮጵያ ውስጥ የሚመነጩ ሰነዶች

1.1.1.     የልደት፣ የጋብቻ፣ ያላገባ/ች፣የፍቺ፣የሞትና የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ ምስክር ወረቀቶች

v     ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ማዘጋጃ ቤትና ከክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች የተሰጡ በቀጥታ ይስተናገዳሉ፡፡

v     ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ማዘጋጃ ቤት የተሰጡ በቀጥታ ይስተናገዳሉ፡፡

v     ከብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የተሰጡ ከሆኑ በክልሉ ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ወይም በክልሉ ደረጃ ስልጣን በተሠጣቸው አካላት ተረጋግጠው  መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     ከክልሎች፣ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ሥር ከሚገኙ የሕክምና ተቋማት የተሰጡ የሞት ማስረጃዎች በከተማ አስተዳደሩ ወይም በክልሎቹ ጤና ቢሮ ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     የጥምቀትና የጋብቻ ማስረጃዎች በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ሲሰጡ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት የተቋማቱ ዋና መ/ቤት ተረጋግጠው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

v     በሃይማኖት ተቋማት የተሰጡ ያላገባ/ች እና የሞት ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

1.1.2.     የትምህርት ማስረጃዎች

1.1.2.1.     የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎች

v     ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የተሰጡ፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣

v     ከአዲስ አበባ  ከተማ መስተዳድር በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የተሰጡ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣

v     ከክልል መስተዳድሮች በመንግስትና በግል የትምህርት ተቋማት የተሰጡ፣ በየክልሉ ትመህርት ቢሮ፣

         ተረጋገጠው መቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5