250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የምትሸፍነው ይህች ከተማ በዛፎች በተሸፈኑ ጋራዎችና እና በወንዞች ፍሰት በተፈጠሩ ሸለቆዎች መሀል ለመሀል ተንሠራፍታ ትገኛለች፡፡ ምንም እንኳ ለምድር ወገብ ቅርብ ብትሆንም አዲስ አበባ ከፍታዋ በዓለም ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጣት አየር ንብረቷ መካከለኛ ማለትም የሙቀት መጠኗ በአሸሬጂ 16oc (61of) በአብዛኛው ሞቃትና ደረቅ የሚባሉት ወራት ሚያዝያና ግንቦት ሲሆኑ በነዚህ ወራት ቀን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ ሞቃት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ ነፍሻማ ነው፡፡ በዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ ቀናትም ማታ ቀዝቃዝ ያሉ ናቸው፡፡ ከጥቅምት እስከ ጥር አጋማሽ የማታዎች አየር ሁኔታ እስከ (40) ይቀዘቅዛል ነገር ግን ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ክረምት ወቅት የሚመጡ ጎብኚዎች የአዲስ አበባን አየር ንብረት እጅጉን ተስማሚ ሆኖ ያገኙታል።፡

 

የአለም አቀፍ ኮንፈረንሶችና ሁኔታዎች አዘጋጅ

ኢትዮጵያ የተለያየ ህጎችን የሚያዘጋጁ፣ በሀገራት እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ፣  አለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን የሚገዙ ህጎች እንዲከበሩ የሚሰሩ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መስራች አባል ናት፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትብብርን በሀገራት መካከል ለማጠናከር የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ጽኑ ዕምነት አላት፡፡

እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባዘጋጁት መድረክ መሠረት ኢትዮጵያ ህጉን ተከትላ በዚህ በግሎባላይዜሽን ዘመን የበኩሏኝ እየተወጣች ነው የምትገኘው፡፡

ስለዚህም ነው እንግዲህ ኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያሉ ሀገሮች የዓለም አቀፍ ጨዋታን ህጎችና የሌሎችን ጥቅም ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለባት የምታምነው፡፡ የሚትዮጵያ ሚና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥም ሆነ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ያላት ትብብር አንዱ ታላቁ የሀገሪቷ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያላት ተሣትፎ አካል ነው፡፡

የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ማለቁን ተከትሎ የተመሰረተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ከላይቤሪያ ጋር በመሆን መስራች ሀገር ናት ኢትዮጵያ እናም የተባበሩት መንግስታት ከተመሰረተ በኋላ ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ሙሉ ቁርጠኛ ሆና ቀጥላለች፡፡ የተ.መ ቻርተር መርሆ የሆነው የጋራ ደህንነት ለኢትዮጵያ ልዩ ትርጉም ያለው ነው ምክኒያቱም ያልተሳካው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ሙከራም ይሄው የዓለምን ሠላም ማስፈን ስለነበረ ነው፡፡ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ በድጋሚ ኢትዮጵያን ከፍሺት ኢጣሊያ ያልታደገበትን ሀላፊነቱን አስመልክተው የሚተቹበት ዝነኛ ንግግራቸው ኋላ ላይ ብዙዎች በዓለም አቀፍ መሰበረሰብ በጸጸት ሲከተላቸው ኖሯል፡፡

የጋራ ደህንነትና ትብብር ሀሳብ እንዲርቅ ያደረገውና የተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሠረት እንዲፈጠር ካደረጉ አንኳር ምክኒያቶች በእርግጥም አንዱ ይህ ነው፡፡

Pages: 1  2