ኤዠያ አገራት ጋር የሚኖረን ግንኙነት

አህጉሩ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የሚኖርበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን የዓለማችን ሁለተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ የሚገኝበት ከፍለ ዓለም   ነው፡፡ በተጨማሪም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገቡ አገራት መገኛ መሆኑና ም በፈጣን እድገት ላይ የሚገኙት ሕንድ እና ቻይና የመሳሰሉት አገራት የሚገኙበት አሕጉር ነው፡፡ በመሆኑም አሕጉሩ በልማታችን ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክት የሚችል በመሆኑም በአህጉሩ ላይ ልንከተለው የሚገባው ፖሊሲ የአሁጉሩ አገራት ለልማታችን እንደ አርዓያነት ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ ማግኘት የምንችለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም አህጉሩ  ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚሄድ የኢንቨስትመንት አማራጭም በመሆን የሚያገለግል ከመሆኑ በተጨማሪም እንደቻይና እና ዻፓን የመሳሰሉት አገራት የእርዳታ እና የብድር በመስጥት ልማታችንን የሚያግዙ የልማት አጋሮቻችን በመሆናቸው  የምንከተለው ፖሊሲ እነዚህን ጥቅሞች ከፍ የሚያደርግ መሆን አለበት።