ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት

ሀገራችን ከአፍሪካ ህብረት ምስረታ እንዲሁም ከፀረ ቅኝ ግዛት ትግሉ ጀምሮ ለአህጉሩ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ጋር ሊኖረን የሚገባው ግንኙነት ትኩረት የሚያደርገው በሰላማችን ላይ በሚኖረው ፋይዳ ላይ ሲሆን፤ ይህንንም ለማረጋገጥ የአፍሪካ ህብረትን መሰረታዊ መርሆዎችንና ግንጭቶችን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ እና በመፈፀም በአህጉሩ ያለንን ተሰሚነት ከፍ ማድረግ ይኖርብናል ፡፡ በተጨማሪም ከአህጉሩ አገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መልካም ግንኙነት በመመስረት የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታችንን የሚያውኩ ጉዳዮችን መቀነስ ይኖርብናል፡፡