መገኛ እና ድንበር

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ መሀከል ስትገኝ ከሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በስተ ምዕራብ፣ ከኤርትራ በስተ ሰሜን እና ምስራቃዊ ሰሜን፣ ከጅቡቲ እና ሶማሌላንድ በስተ ምሥራቅ እና ከኬንያ እና ሶማሊያ በደቡብ ድንበር ትጋራለች፡፡ 1.14 ሚሊዮን ስኩየር ኪ.ሜ. /994000 ስኩዬር ማይልስ/ የቆዳ ስፋት ሲኖራት የሕዝብ ብዛት በ2000 ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ መሠረት 73‚918‚505 ሲሆን የእድገት ፍጥነት ደግሞ 3.2% እና በአሁኑ ወቅት ያለው የሕዝብ ብዛት 86 ሚሊዮን ሲገመት 46% ከ1-14 ዕድሜ ክልል፣ 51% ከ15-64 የዕድሜ ክልል እና 3% ደግሞ ከ65 ዓመት በላይ ናቸው፡፡  በአጠቃላይ 17% የሀገሪቱ ሕዝብ በከተማ አካባቢዎች ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡

 

ብሔር እና ብሔረሰቦች

ኢትዮጵያ ከ80 ለሚበልጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ ስትሆን በ2000 ዓ.ም. በተደረገው ሕዝብ እና ቤት ቆጠራ መሠረት የኦሮሞ ሕዝብ 25.5 ሚሊዮን /35%/፣ የአማራ ሕዝብ 20 ሚሊዮን /27%/፣ የሶማሌ ሕዝብ 4.6 ሚሊዮን /6.2%/፣ የትግራይ ሕዝብ 4.5 ማሊዮን /6.1%/፣ የሲዳማ ሕዝብ 3 ሚሊዮን /1.7%/፣ የአፋራ ሕዝብ 1.3 ሚሊዮን /1.7%/ እና የጋሞ ሕዝብ 1.1 ሚሊዮን /1.5%/ ናቸው፡፡

 

ሐይማኖት

የክርስትና እምነት ተከታዮች ከጠቅላላው የሕዝብ ብዛት 62.8% /43.5%/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና 19.3 ሌሎች/፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች 33.9%፣ የባህላዊ እምነት ተከታዮች 2.6% እና ሌሎች 0.6% በመሆን ይኖራሉ፡፡

 

የአየር ፀባይ

ኢትዮጵያ በ15 ዲግሪ ሰሜናዊ የምድር ወገብ ብትገኝም በአጠቃላይ ሀገሪቷ በመሀከለኛ እና ምቹ የአየር ሁኔታ ሲኖራት አልፎ አልፎ 20 ዲግሪ ሴንቲግሬድ /68 ዲግሪ ፋራናይት/ ይደርሳል፡፡  በሳሳ ሁኔታ የተበታተኑ ሕዝቦች የሚገኙበት የሀገሪቱ ዝቅተኛው ክፍል ሞቃታማ የአየር ጠባይ ሲኖረው የአፋር ክልላዊ መንግሥት በሀገሪቱ ምሥራቅ ከባህር ወለል በታች ከምድር ላይ ካሉ አካባቢዎች ሞቃታማ በመሆን 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ //120 ዲግሪ ፋራናይት/ እና በላይ የአየር ሁኔታ አለው፡፡

የሀገሪቱ አማካይ አመታዊ የዝናብ መጠን 850 ሚሊ ሜትር /34 ኢንች/ ሲሆን ለአለማቀፍ ደረጃ ምቹ ተብሎ ይታሰባል፡፡  በአብዛኛው የሀገሪቱ ከፍተኛ ቦታዎች ዝናብ በሁለት ወቅቶች ሲከሰት፡-

  •  አነስተኛ ዝናብ /በልግ/ በየካቲት እና መጋቢት ወራቶች
  •  ከፍተኛ ዝናብ /ክረምት / ከሰኔ እስከ መስከረም

በደቡባዊ ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች የዝናብ ወቅት     ከመጋቢት እስከ ግንቦት ወራት ሲሆን ረጅሙ ወቅት እና አጭሩ ወቅት ደግሞ ከጥቅምት እስከ ታህሣሥ     ይሆናል፡፡

 

ኮሙኒኬሽን

በሀገሪቱ አለም አቀፍ ኤርፖርቶች በአዲስ አበባ/ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት/ እና በድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ ጐንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱም፣ አርባምንጭ እና መቐሌ ሲገኙ በብሔራዊ አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ክብርና ተቀባይነት ሲኖረው በአሁኑ ወቅት ወደ 81 አለም አቀፍ መዳረሻዎች አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አፍሪካና ኤሽያ እና 18 አገር አቀፍ መዳረሻዎች አሉት፡፡  በአሁኑ ወቅት የድሪም ላይነር 787 ቦይንግ አውሮፐላን በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡ ዋና የመግቢያ ቦታዎች በሞያሌ /ከኬንያ/፣ ሁመራና መተማ /ከሱዳን/፣ ደወሌ /ከጅቡቲ/፣ ሲሆኑ ሁሉም ሙሉ የጉምሩክና የኢሜግሬሽን ማጣሪያ አላቸው፡፡ከ1998 የኤርትራ ወረራ በፊት ሁመራ፣ ራማ፣ ዛላምበሳና ቡሬ ከኤርትራ መግቢያ  ሆነው ያገለግሉ የነበረ ሲሆን በኤርትራ መንግሥት በኩል ምንም አይነት የሀገሪቱን ግንኙነት ለማስተካከል የተደረገ ጥረት ስለሌለ በአሁኑ ወቅት አገልግሎት አይሰጡም፡፡

 

ቪዛ

ከኬንያ ዜጐች በስተቀር ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ጐብኚ ቪዛ ሲያስፈልገው ይህም ቪዛ ቀደም ብሎ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ለ1 ግዜ፣ ከ1-3 ወራትና ቱሪስት ቪዛ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ይሰጣል፡፡  ለተጨማሪ መረጃ የቢዝነስ ወይም የተለያዩ የቱሪስት መግቢያ ቪዛዎችን በተመለከተ በአቅራቢያ የሚገኝ የኢትዮጵያ ኤምባሲን በመጠየቅ አስፈላጊ ፎርሞችን ማግኘት ሲቻል የተሰጡት ቪዛዎች የሚያገለግሉት ከተሰጡበት ቀን እንጂ ኢትዮጵያ ከተደረሰበት ቀን ጀምሮ አይደለም፡፡