Back

የአፍሪካ ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የአፍሪካ ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የአፍሪካ ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሀላፊነት የኢትዮጵያን ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጐቶች ከጐረቤት አገር ጋር ባሉን ግንኙነቶች እና ከሌሎች አፍሪካ አገራት ጋር በምናደርጋቸው ግንኙነቶች ማስጠበቅ ነው፡፡ ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ ከጐረቤት አገሮች ጋር ጥሩ ጉርብትና ለመፍጠርና የተፈጠረውን ጥሩ ግንኙነትም በአፍሪካ ቀንድ እየተካሄደ  ያለውን አንድነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዲያደግ ለማድረግ ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡ ከሌሎች ባለድሻ አካላት ጋር በመሆን አስተማማኘ እና ቀጣይነት ያለው ሰላምነም በማረጋገጥ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማምጣት ከሌሎች ዳይሬክቶች ጋር በመሆን ይሠራል፡፡ በተጨማሪም ፕሮግራሞችን በመንድፍ እና በማስፈጸም የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታትን ለማጠናከር ይሠራል፡፡

የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ኢትዮፅያን በመወከል በአገራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋል፡፡ ከሚመለከታችዉ አካላት ጋር በመተባበር ስለኢትዮጵያ በየተባበሩት መንግስታት እና አፍሪካ ሰላም አስከባሪ ዘመቻ በተመለተ አስፈላጊውን ተግባር ይከውናል፡፡  በሰነዓ ፎረም፣ በኢትዮ-ሱዳን እንዲሁም የግብጽ የሶስተዩሽ ፎረሞች እንዲሁም የተ.መ. ድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ትብብሮች እና የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የአፍሪካ ልማት እርዳታ ያስተባብራል፣ እንዲሁም የCOMESAን የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና ፓለቲካዊ እና የደህንነት እንቅስቃሴዎች ይከታተላል በተጨማሪም የአፍሪካ ትብብር ጉባኤዎችንም ያስተባብራል፣ የኢትዮጵያን አገራዊ ጥቅሞችም በሌሎች አህጉራዊ ተቋማት ላይ ያስጠብቃል፡፡

ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ ከሎሎች አፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን ግንኙነት በማጥናት በንግድ፣  ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንት በኩል ያሉ የትኩረት አቅጣጫዎችን ይለያ፡፡ እንዲሁም የሁለትዬሽ እና አካባቢያዊ ስምምነት (treaties) ይፈራረማል ብሎም ኢንቨስትመንት ወደ ሀገራችን እንዲደረግ፣ የውጭ ንግድን ለማሳደግ እንዲሁም በስልጠና እና አቅም ግንባታ ረገድ ያሉ ትብብሮችን ለማቀናጀት የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡

የኢኮኖሚና የቢዝነስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራልንም ስለተገኘ የገበያ እድሎች እና የስልጠና ሂደሮች መረጃዎችን ይሠጣል በተጨማሪም ኮንፍረንስ ቱሪዝምን ለማሳደግ እና ለማስተዋወቅ አስፈላጊውን መረጃ ይሠበስባል ያጠናቅራል፡፡

የፓሊሲ ጉዳዬችን በተመለከተ፣ ጉብኝቶችን እና ሌሎችንም የሚመለከተውን እንቅስቃሴዎች በተመለከተ ጥናት ያደርጋል እንዲሁም አማራጮችን ይጠቁማል በተጨማሪም የመነጋገሪያ ነጥቦችን ያዘጋጃል፡፡ በተከታታይ ከተለያዩ አገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዬች ጋር በመገናኘት በአገራችን እየተመዘገቡ ስላሉ ልማቶች በመወያየት የአገራችንንም ፍላጐት ያስተዋውቃል፡፡ በአፍሪካ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖችን እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል በተጨማሪም ከአፍሪካ ሀገራት አህጉራዊ እና ክልላዊ ተቋማት ተወካዩች ጋር በተከታታይ የጋራ ፓለቲካዊ ጉዳዩችን ይወያያል፡፡

የአፍሪካ ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የፕሮቶኮል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል