Back

የፕሮቶኮል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የፕሮቶኮል ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ክፍል (ቢሮ) የሀገሪቱ የፕሮቶኮል ክፍል ሆኖ ያገለግላል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ክፍል ኃላፊነት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከውጭ አገራት ርዕሰ ብሔራንና የአገራት መሪዎች እና ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የውጭ አገራት የዲፕሎማሲ ተወካዮች ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት ማሰናዳትንም የካትታል ።

የፕሮቶኮል ክፍል በኢትዮጵያ የሚደረጉ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉብኝቶችንና አገራዊ ስነ-ስርዓቶችን (ዝግጅቶችን) እንዲሁም ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ጉባኤዎችን፣ ስብሰባዎችንና ሸንጎዎችን (ፎረምችን) የማዘጋጀት ኃላፊነት አለው።

ክፍሉ የውጭ አገራት የዲፕሎማሲና  የቆንስላ ተልዕኮዎችን እና ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ  ድርጅቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይይዛል፣ እ.ኤ.አ. የ1961 በዲፕሎማሲ ግንኝነት ላይ ስምምነትንና እ.ኤ.አ. የ1963 በቆንስላ ጉዳዮች ላይ ስምምነትን ተፈጻሚነት ይቆጣጠራል። የዲፕሎማቶች ልዩ መብትንና ከለላን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ም ይከታተላል።

 

የፕሮቶኮል  ክፍል ቅርፅ

የፕሮቶኮል  ቢሮ ሁለት ዳይሬክትሬቶች  (ዋና ክፍሎች) አሉት። እነሱም አገራዊ የስነ-ስርዓትና ፕሮቶኮል ዳይሬክቶሬት እና የልዩ መብት፣ የከለላና የማስታረቅ ዳይሬክቶሬት ናቸው።

አገራዊ የስነ-ስርዓትና ፕሮቶኮል ዳይሬክቶሬት በዋናኝነት  የፕሬዚዳንቱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ተግባራት ይከታተላል። ዳይሬክቶሬቱ  ከላይ የተጠቀሱትን ሚነስትሮች በውጭ አገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት እንዲሁም የውጭ አገራት ርዕሳነ-ብሔሮች ፣ የአገራት መሪዎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ ጉብኝት ያዘጋጃል፤ ያቀናጃልም።

ዳይሬክቶሬቱ በኢትጵያ የሚካሄዱ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ጉባኤያትን ያዘጋጃል፤ በተጨማሪም የአምባሰደሮችን የሹመት ደብዳቤ የማቅረብ ስነ-ስርዓት፣ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ኃላፊ የሹመት ደብዳቤ አሰጣጥና ሽኝት (ስንብት) ጉብኝት ዝግጅትን፣ የወታደር አታሼ አቀባበል ቅንጅትን እንዲሁም ለተልዕኮዎች ኃላፊ የተጠየቁ ቀጠሮዎችንና የውጭ አገር የመንግስት ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት የሚያቀርቡትን የጉብኝት ጥያቄ የተመለከቱ ስራዎችን ያከናውናል።  

 የልዩ መብት፣ የከለላና የማስታረቅ ዳይሬክቶሬት

ዳይሮክቶሬቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚተገበሩ ልምዶች እና አገሪቱ (አስተናጋጅ አገር) ውስጥ ባሉ ህጎች እና ደንቦች ላይ በመመርኮዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የውጪ አገራት  የዲፕሎማሲና የቆንስላ ተልዕኮዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሰራተኞቻቸው የሚሰጡ ልዩ ልዩ የዲፕሎማሲ መብቶች እና ከለላዎችን ይቆጣጠራል።

ዳይሬክቶሬቱ የውጭ አገራት ተዕኮዎችን፣ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ድርጅቶችን ይመዘግባል። የተሽከርካሪ ምዝገባን፣ የመንጃ ፈቃድን እና የቀረጥ (የጉሙሩክ) ፈቃድን ያስተባብራል። የገንዘብ ልዩ መብቶች አያያዝም የዳይሬክቶሬቱ ኃላፊነት ናቸው። በተጨማሪም በዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች፣ በዓለም አቀፍና ቀጠናዊ  ድርጅቶች፣ በሰራተኞቻቸው እና በኢትዮጵያ ዜጎችና በህግ አካላት መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን የመፍታት ሥራዎችን ያከናውናል። 

ሁለቱም ዳይሬክቶሬቶች ተጠያቂነታቸው  በቀጥታ ለዋና የፕሮቶኮል ክፍል ነው።