Back

የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል

የኢኮኖሚና የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ለመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ለቢዚነስ ማኅበረሰብ  ታዓማኒ፣ ትክክለኛና ጊዜውን የጠበቀ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ሁኔታዎችን እና የገበያ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የማቀናጀት እና ወደ ሥራ የማስገባት ኃላፊነትን ይወጣል።

ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ የንግድ ማኅበረሰቡንና የመንግስት የፍላጎት መስኮችን ይለያል። ንግድንና ቱሪዝምን የተመለከቱ መረጃዎችን ያሰራጫል፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችንንና የቱሪዝም መስህቦችን  ለማስተዋወቅ መርኃግብሮችን ይቀርጻል ድጋፍንም ያደርጋል እንዲሁም የቢዝነስ ስምምነቶችን (ህጎችን) ያግዛል ግንኙነቶችንም ያመቻቻል። በውጭ ንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች መለየት፣ ግጭቶችን በመፍታት ሂደት ዕገዛን ማድረግ፣ የገብያ ዕድሎችን ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ከሁለትዮሽና ከብዙኃን የግንኙነት ምንጮች ጋር በመሆን የአቅም ግንባታ መረኃግብሮችን ማዘጋጀት እንዲሁም በድንበር ተሻጋሪ ንግድ፣ በደቦችና የመተላለፊያ አጠቃቀም ስምምነቶች ላይ የሚደረጉ ሥራዎችን ማገዝ ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ ሥራዎች ናቸው። ለአገር በቀል አስጎብኚ ደርጅቶች ከውጭ አገራት አቻዎቻቸው ጋር በማስተባበር፣ የጎብኚዎችን ቁጥር ለመጨመር በመስራት፣ በቡድን ለሚመጡ ጎብኚዎች ቪዛን በማቅረብና መረጃን በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ስብሰባዎች በኢትዮጵያ  እንዲደረጉ በመቀስቀስ የስብሰባ ቱሪዝምን ያበረታታል።

በውጭ ከኢትዮጵያ ተልዕኮዎችና ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት  ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በመለየት እና ትክክለኛ ባለሀብቶችን በመምረጥ ይሰራል፣የማስታወቅያ ሠነዶችን በማዘጋጀትና በውጭ የኢትዮጵያ ተልዕኮዎች የሚገለገሉበት የመረጃ ክምችት የማዘጋጀት ሥራዎችን ይሠራል። የብድር፣ የዕርዳታና የቴክኒካዊ ትብብር ስምምነት መረጃዎችን ይተነትናል፣ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መረጃ ይሰጣል እንዲሁም በቢዝነስ የትኩረት መስኮች አጋሮችን በአስፈላጊነት ደረጃ ይለያል። አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን በማመዛዘን የሌሎች አገራት የልማት ድጋፍ ተሞክሮዎችን ያጠናል ።

የኢኮኖሚና የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የጋራ ጥቅሞችን የሚያስጠብቁ  ትብብሮችን ለመፈጸም እንዲረዳ የጎሮቤት አገራት ፖሊሲዎች ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን በጥልቀት ይመረምራል።የወደብ አልባ አገራት ቀጣይነት ያለው የወደብ አጠቃቀምን በተመለተ ያላቸውን አቋም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያቀርባል።  የቡድን 8  የድርጊት ዕቅድ (አክሽን ፕላን) አፈጻጸምና የልማት አጋሮች የODA ደረጃዎችን ለማሳደግና የዕዳ ጫናን ለመቀነስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ይከታተላል። በዝቅተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ያሉ አገራት (LDCs) የልማት ችግሮችን ለመፍታት የተነደፈውን የብራስልስ የድርጊት መረኃ-ግብር አጠቃቀመምና ኢትዮጵያ በዝቅተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ያሉ አገራት (LDCs) ጉዳዮች የአፍሪካ ቡድን፣ በቡድን 8ና በተባበሩት መንግስታት የምትጫወተውን ሚና ማሳደግም ሌሎች የትኩረት ዘርፎች ናቸው።

ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ የኢኮኖሚና ዲፕሎማሲን ለማበረታታትና መረጃዎችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው የውስጥ የድርጊት ቡድን ለማቅረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በመወከል በጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ላይ ይሳተፋል። የአፈጻጸም ሪፖርቱን ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል በየጊዜው ያቀርባል።