Back

ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሚዩኒኬሽን ዳ/ጄ

ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሚዩኒኬሽን ዳ/ጄ

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የአገራዊ እና አለም አቀፉን የመገናኛ ተቋማት እንዲሁም ሰፊውን ህዝብ ስለኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፓሊሲ እና የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች ማስገንዘብ እና የማሳወቅ ተግባራትን ይከዉናል ፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የኢትዮጵያን ገጽታ ለመጠበቅ እና ለመገንባት ጊዜውን የጠበቀ እና ትክክል መረጃ ለመገናኛ ብዙሀን (Media) ይሠጣል። የሚዲያ መግለጫዎችን እና አቋሞችን እያዘጋጀ ለአገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ ሚዲያ ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሀን ስለኢትዮጵያ የሚያወጡትን ዘገባ እና መግለጫ በመከታተል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ምላሽ ይሠጣል፡፡

ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና አገራዊ መግባባትን ለማስፈን እንዲሁም ሚኒስቴር ጽ ቤቱ የበለጠ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የበኩሉን ጉልህ ድርሻ ይጸጫወታል:: በተጨማሪም በዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጉዳዮች ዙሪያ ለአካባቢዉ: ለከፍተኛ ተቃማት እና ለንግዱ ማህበረሰብ መግለጫወችን ይሰጣል::

በሚኒስቴር ጽ/ቤቱ ዉስጥም ዳይሬድቶሬት ጄኔራሉ ለሚኒስቴር ጽ/ቤቱ ሰራተኞች አለም አቀፍ እና አገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መገለጫወችን ይሰጣል:: በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ዲፓርትመንቶች ስለሚከናወኑ ተግባራትም መረጃዎችን እና ግንዛኔወችን ያሰራጫል:: ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ በተጨማሪም በአጠቃላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድህረ ገፅ የመቆጣጠር ተግባርም ይከዉናል::