Back

የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

(Sep 29, 2015) የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ መስከረም 17 ቀን 2008 ተከብሮ ዋለ። የደመራ በአል በተለይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።

በዓሉ መከበር የጀመረው እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀበለበት መስቀል በመቀበሩና  በቆሻሻ  ክምር  በመሸፈኑ፥  ንግስት እሌኒ የተደበቀውን መስቀል ለመፈለግ በቁፋሮ ወቅት የተጠቀመችን ደመራና የእጣን ጭስ  ለማመላከት ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት፥ የመስቀል በዓል የመዳን ምክንያት፣ የፍቅር እና ወዳጅነት ምልክትም ተደርጎ ይከበራል ብለዋል።

የዘንድሮው በዓል የግብጹ እስክንድርያ ጳጳስና የመንበረ ማርቆስ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ባለበት እና የመስቀል በዓል በዓለም ቅርስነት በተመዘገበ ማግስት መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ በጎንደር ከተማ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይም ታድመዋል፡፡ 

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ታዎድሮስ ዳግማዊ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገልጸዋል።