ፕሬዝደንት ኦባማ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸዉ ተሸኙ

(ሐምሌ 21፣2007) (Jul 30, 2015) ለይፋዊ ጉብኝት ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ የነበሩት የአሜሪካው ፕሬዝደንት  ባራክ ኦባማ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አሸኛኘት ተደረገላቸው::

ባራክ ኦባማ ባለፈው እሁድ ምሽት አዲስ አበባ በመግባት ከፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እንዲሁም ከጠቅላይ ሚንስትር ሃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል:: በተጨማሪም ፕሬዝደንቱ  የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎችና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል::

በቤተ መንግስት ተገኝተውም ሉሲን ጎብኘተው በአማረ የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነ-ስርኣት ታጅበው ቡና ጠጥተዋል በተደረገላቸው ደማቅ መስተንግዶ መደሰታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል::

ፕሬዝደንቱ ኢትዮጵያ ከአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ የገዛችውን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ጎብኝተዋል::

ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለ ማርያም እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፕሬዝደንቱን ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ሸኝተዋቸዋል::