የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ ሐምሌ 02 ቀን 2012 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ . . .
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየቃል አቀባይ /ቤትሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫሀሙስ ሀምሌ 2 ቀን 2012 ..አዲስ አበባ

መግቢያበዚህ ዓመት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ መከሰቱን ተከትሎ እንዲሁም በአገራችን ከመጋቢት ወር 2012 አጋማሽ ጀምሮ ወረርሽኙ በመከሰቱ የተነሳ የመሰብሰብ ክልከላ/ገደብ በመጣሉ ምክንያት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመደበኛነት ይሰጥ የነበረው ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ተቋርጦ መቆየቱን በማስታወስ፤ ይህንን ክፍተት ለመሙላትም የአንድ ለአንድ ቃለ ምልልስ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በጽ/ቤታችን በኩል በስፋት በመስጠት ከመጃ ተደራሽነት አንጻር ሊፈጠር ይችል የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ሲሰራ መቆየቱን፤ ምንም እንኳ በአሁኑ ስዓትም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት በአገራችን እየጨመረ የሚገኝ ቢሆንም ጉዳዩ New Normal ሆኖ የቀጠለ በመሆኑ፤ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫውን ማስቀጠል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በጽ/ቤታቱ ከዛሬ ጀምሮ በቋሚነት /በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የሚሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት መጀመሩን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት በዛሬው እለት በመ/ቤታችን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዘመን በመከናወን ላይ ያሉትን የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎችን ማለትም ሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚና ቢዝነስ ዲፕሎማሲ እንዲሁም የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መግለጫ ተሰጥቷል።

አምባሳደር ዲና ወደ ዋናው መግለጫ ከመግባታቸው በፊት ባለፈው ሳምንት በታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ ተጫዋች ተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት እንዲሁም የእርሱን ሞት ተከትሎ በተፈጠረው ግርግር ለሞቱ ኢትዮጵያዊያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በራሳቸውና በቃል አቀባይ /ቤት ስም
በድጋሜ ልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወዳጁ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በአገራችን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓም ኢዲስ አበባ ለሚገኘው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መግለጫ መሰጠቱንም አምባሳደር ዲና አንስተዋል። ከግድያው ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በሚመለከተቻው አካላት ቀጣይ ዝርዝር ጉዳዮቸ ተጣርተው በቂ መረጃ ሲገኙ ደግሞ በየደረጃው ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንደሚገለጽም አምበሳደር ዲና አሳውቀዋል።

 1. ከሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በአገራችን እየተደረጉ ያሉ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስራዎች በተመለከተ

ሁሉም እንደሚያውቀው በዓለም ላይ በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር በመንቀሳቀስ የሚደረገው የዲፕሎማሲ ስራ በእጅጉ መገደቡን፤ ይሁን እንጂ በቨርቿል ቴክኖሎጂ እና በቴሌ ኮንፈረንስ በመጠቀም እንዲሁም የእንድ ለአንድ ውይይቶችን በማጠናከር ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ የዲፕሎማሲ እንቅቃሴዎች በስፋት ተጠናክረው መቀጠላቸውን አመባሳደር ዲና ገልጸዋል።

 • ለአብነት ያህል የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትት ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሰኔ ወር ብቻ ያደረጓቸውን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች አንስተዋል፤
  • ክቡር አቶ ገዱ በሰኔ ወር ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ክቡር ሙሳ ፋኪ ማህመት እንዲሁም ከምክትል ኮሚሽነራቸው ክቡር ኳርተይ ቶማስ ከዌሲ ጨምሮ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ የአንድ ለአንድ ውይይቶችን በማድረግ ከየአገራቱ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ የማስቀጠል ሰራዎቸ መሰራታቸውን፤ በተመሳሳይ ክቡር አቶ ገዱ በወሩ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን አዲሰ አበባ ካደረጉ የስዊድን፣ የፊንላንድ፣ የሳኡዲ አረቢያ፣ የኔዘርላንድስ፣ የሩሲያ አምባሳደሮችን በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር፣ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ እና ሌሎችንም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን፤

  • የቨርቷል ቴክኖሎጅን እና ቴሌ ኮንፈረንስን በመጠቀም በሰኔ ወራት ብቻ ከተባበሩት አረብ ኤሚሪቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ጋር፣ ከጣሊያን
   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሉይጊ ዲማዮ
   ጋር፣ ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ዩንግ ውሃ ጋር፣ ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ጋር የአገራቱን ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በርካታ ውይይቶችን አድርገዋል። በነዚህ ውይይቶችም አገራቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይብልጥ አጠናክረው ለማስቀጠል መስማማታቸውን፤

  • ከዚህ ባለፈ ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችን በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንበታ ጋር በተያያዘ እያደረጉ ባሉት የቬርቿል ኮንፈረንስ ላይ  የኢትዮጵያን አቋም በተመለከተ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ኢትዮጵያዊያኑ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን፤

  • ሚሲዮኖቻችንም በተመሳሳይ የቨርቿል ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት ይሰሯቸው የነበሩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በስፋት አጠናክረው መቀጠላቸውን አመባሳደር ዲና በመግለጫቸው አንስተዋል።

1.1 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንበታ የሶስትዮሽ ውይይትና ድርድር ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ

 • የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንበታና የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት
  • ሁሉም አንደሚያውቅው በዚህ በጀት ዓመት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በርካታ ተከታታይ ውይይቶችንና ድርድሮችን ማድረጋቸውን፤ ድርድሮችንና ውይይቶችን ተከትሎ ግብጽ ..
   ሜይ 1 እና ጁን 19 ቀን 2020 የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን በተመለከተ አገራችንን በመወንጀል ለተ.. የፀጥታው ምክር ቤት ሁለት አቤቱታዎች ማቅረቧን፤  በተመሳሳይ ሱዳን
   በህዳሴው ግድብ ላይ አጠቃላይ ስምምነት ሳይደረስ ሙሌት እንዳይጀመር በሚል .. ጁን 2 ቀን 2020 ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ማስገባቷን፤

  • ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያም በሁለቱም አገራት በኩል ለቀረቡ አቤቶታዎች ምላሽ የሚሆን ሰነድ ተዘጋጅቶ ለጸጥታው /ቤት እንዲደርስ
    ማድረጓን፤ በተጨማሪም የአገራችንን አቋምን 5 የተመድ
   ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ የፀጥታ ምክር ቤት አባል አገራት እንዲያውቁት ማድረጓን፤ ይህንን ተከትሎም የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ... ጁን 29 ቀን 2020 Open Debate
   አድርጓል፤ የም/ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን መስጠታቸውን፤ አገራችንም አቋሟን አሳውቃለች፤ በመጨረሻም Consensus ጉዳዩ በአፍሪካ ምድር አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት መግባባት የተደረሰበት ሁኔታ መፈጠሩን አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።

 • ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት እየተደረገ ስለሚገኘው የሶስትዮሽ ውይይት

  • የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ...
   ከጁን 09 እስከ 17 ቀን 2020 በሱዳን እና ግብጽ ጥያቄ መቋረጡን በማስታወስ፤ ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ቢሮ ... ጁን 26 ቀን 2020 Virtual
   conference ማካሄዱን፤
   በስብሰባው ከናይል እና ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንደሚሹ ከግንዛቤ በማስገባት ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በቀሪ ጉዳዮች ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከስምምነት እንደሚደርሱ መግባባት መቻላቸው፤ በዚሁ መሠረት በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት (AU-Led
   Process) የሶስቱ
   አገራት የቴክኒክ ውይይት በውሃ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ደረጃ ... ከጁላይ 03 ቀን 2020 ጀምሮ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ፤ በዚህ በስብሰባ ላይ ደቡብ አፍሪካ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑበሊክ፣ ማሊ እና ኬንያ የአፍሪካ ሕብረት ቢሮ አባላት በመሆናቸው በታዛቢነት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንን በመወከል ከደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ማዳጋሰካርና ዚምባብዌ የተውጣጡ የቴክኒክና የህግ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት መሆኑን፤ ... ጁላይ 03 ቀን 2020 ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የሶስትዮሽ ውይይት ሶስቱም አገራት ያላቸውን concern ማቅረባቸውን፤ በመቀጠልም ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድርድር ሂደት በሚመለከት አዲስ ለተካፈሉት ታዛቢዎችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ገለጻ መሰጠቱን፤ ስለሆነም ከዚህ ቀደም በተደረጉ ድርድሮች ስምምነት የተደረሰባቸው እና ተጨማሪ ውይይት የሚፈልጉት ጉዳዮች ላይ ገለፃ እና ውይይቶች መካሄዳቸውን፤ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና የግብጽ ተደራዳሪዎ በተናጠል ከታዛቢዎች ጋር እንዲወያዩ ተደርጎ ውይይቱ እየተካሄደ እንደሚገኝ አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው አንስተዋል።

         2. ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በተመለከተ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች

 • ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር / አብይ
  አህመድ የሚመራው  የለውጥ አመራር
  ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ የዜጎቻችን ጉዳይ ቁጥር አንድ ቁልፍ ስራ ተደርጎ በመሰራት ላይ ያለ ጉዳይ መሆኑን፤ በዚሁ መሰረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም በተለይ አሁን ባለው የኮቪድ ወረርሽኝ ዘመን ራሳቸውን ከኮሮና ወረርሽኝ ከመጠበቅ ባሻገር ለአገራቸው የሚያደርጉትን ልዩ ልዩ ድጋፍ አጠናከረው የቀጠሉበት ሁኔታ እንዳለ፤ ከዚህ ባለፈ ዜጎቻችን በሚኖሩበት አገር ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲፈልጉ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅትና ጥንቃቄ ተደርጎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን፤ ለአብነት ያህልም የኮቪድ 19 በአገራችን ከተከሰተ ከመጋቢት ወር አጋማሽ ወዲህ ከሳኡዲ አረቢያ፣ ከቤሩት /ሊባኖስ፣ ኩዌት እና ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንዲመለሱ መደረጉን፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት 287000 በላይ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን፤ ይህም ሆኖ ግን በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ዜጎቻችን ኡህንም ድረስ ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ሲያሳዩ መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

 • ይሁን እንጂ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሰዎችን ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር በብዛት የሚደረግ ዝውውር በእጅጉ እንዲገደብ፤ ዝውውር የግድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በውሳኔ ቁጥር A/RES/73/195 ባፀደቀው ውሳኔ፣ የተ.. የሰብዓዊ
  መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር /ቤት በሰብዓዊ መብት እና ህገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ጉዳይ ባዘጋጀው የመርህና መተዳደሪያ ምክረ ሃሳብ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዜጎችን ከአገር በብዛት አስገድዶ ማስወጣት የሰው ልጅን ሰብአዊ መብት በመጣስ ለጤና እክል ከማጋለጡም በላይ የተቀባይ አገራት ላይ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ አገራት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ መግለጹ እንደሚታወቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ካላቸው የስራ ባህሪ አንጻር በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስራ በማቆማቸው ለተለያዩ ችግሮች በእጅጉ ተጋልጠው እንደሚገኙ፤

 • በመሆኑም የዓለም አቀፍ ተቋማትን ስጋት እና ማሳሰቢያ እንዲሁም የዜጎቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ተጋላጭነት ምክንያት ከሚኖሩበት አገር ወደ አገራቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዜጎቻችን ክብራቸው ተጠብቆ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት / ጽዮን
  ተክሉ የሚመራ 11 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቋቁመውና በሰላም ሚኒስቴር ከሚመራው ግብረ ሃይል ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ፤ ኮሚቴው ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ አገር ቤት እንዴት ይመለሳሉ፣ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ እስከ መኖሪያ ቀያቸው ድረስ ከህብረተሱ ጋር እንዴት ይዋሃዳሉ የሚሉና በሌሎች መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ከሰላም ሚኒስቴር እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ከሚገኙ የኢፌዲሪ የሚሲዮን መሪዎች ጋር፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ካደረጉ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሃላፊዎች ጋር፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አምባሳደሮች ጋር፣ ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደር፣ የተ.. ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያ አስተባባሪ እና የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች አድርጓል፤ ዜጎች ባሉበት አገር የሚረዱበትን ሁኔታም የማመቻቸት ስራ ሰርቷል። ከዚህ ባለፈ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ወደ አገር ተመላሽ ዜጎቻቸንን ዝርዝር መረጃ የማሰብሰብ ስራ መስራቱንና በዚህ መሰረት ከሳኡዲ አረቢያ፣ ከቤይሩት /ሊባኖስ፣ ኩዌት እና ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንዲመለሱ ተደርጓል መደረጉን፤በቀጣይም ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክያንት ከተለያዩ አገራት እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎቻችን በመለየት ለማስመለስ አስፈላጊው ክትትል የሚደረግ መሆኑን አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።

         3. የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ

በዋናነት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የውጭ ኢንቨስትሮች እንቅስቅሴ እንዳይቀዘቅዝ አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን፤ለዚህም ከዚህ በፊት የነበረውና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚንቀሳቀስው የቅንጅት ኮሚቴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማድረግ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ አምባሳደረ ዲና በመግለጫቸው አብራርተዋል።
Back to Home

More Trade Events ..

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ ሐምሌ 02 ቀን 2012 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ . . . Read More


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ ሐምሌ 02 ቀን 2012 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ . . . Read More


አቶ ነብያት ጌታቸው በዛሬው እለት በተለያዩ ጉዳዮቸ የሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ Read More


የመጋቢት 06 ቀን 2011 ዓ.ም የቃል አቀባይ ጽ/ቤት - ሳምንታዊ መግለጫ Read More


የቃል አቀባይ ጽ/ቤት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ Read More


Read More

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   248
THIS WEEK:   14685
THIS MONTH:   46226
THIS YEAR:   123323
TOTAL:    466013
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Regions
      * Neighboring Countries
      * African Countries
      * Middle East Countries
      * Asia Countries
      * Europe Countries
      * United State of America
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts