" ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አኩሪ ተግባር እንደሚፈጽሙ ዝነኛው ገጣሚ ለምን ሲሳይ ተምሳሌት ነው" ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነግጥም ሎሬት እና የማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ለምን ሲሳይ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ

(23-04-2022 published)
(ሚያዝያ 15 ቀን 2014ዓ/ም አዲስ አበባ)በፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣ በቅርስ ማስመለስ እና በገጽታ ግንባታ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ተናግሯል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለምን ሲሳይ በቅርቡ ከብሪታኒያ መንግስት የኦሪየንታል ብሪትሽ ኢምፓየር/OBE/ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነ ግጥምና በጎ ተግባር ላበረከተው አስተዋጽኦ የእንግሊዝ መንግስትን ከፍተኛ ኒሻን ተሸላሚሆኗል።
ይህን ተከትሎ ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው በጥረቱ ያሥገኘው የክብር ኒሻን ለሌሎች በውጪ ሀገር ለተወለዱ ኢትዮጵያዊያን አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን በመገንዘብ የእንኳን ደስ ያለህ ዝግጅት አካሂዷል።
በእለቱ በተካሄደው ዝግጅት በለንደን የኢትዮጵያ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አኩሪ ተግባር እንደሚፈጽሙ ለምን ሲሳይ ተምሳሌት ነው ብለዋል ፡፡
አያይዘውም ሀገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ መግባባትንና ይሁንታን ለመፍጠር መላው ህብረተሰቡን ያሳተፈ ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን እንደተቋቋመ ገልጸው በውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለኮሚሽኑ ስራ ድጋፍ በመስጠት ለስኬቱ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያ ላቀረበቸው ሀገራዊ ጥሪ ዳያስፖራው በተለያየ ዘርፍ ሙሉ ድጋፉን እንደሰጠ ሁሉ ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለምን ሲሳይ በበኩሉ ኤምባሲው ላደረገለት ዝግጅት እና ዲፕሎማቶቹ ላሳዩት ልባዊ
አክብሮት ምስጋና አቅርቧል፡
ኤምባሲው ሀገሬን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳይ ያደረገልኝ ድጋፍ የማይረሳ እና ማንነቴን ፈልጌ እንዳገኝ ከፍተኛ እገዛ ያደረገልኝ በመሆኑ ከኤምባሲው ጋር የበለጠ ተቀራርቤ ለመስራት ሙሉ ፍላጎት እንዳለኝ አረጋግጣለሁ ብሏል ።
በቀጣይም ያለውን ታዋቂነትና ተጽእኖ ፈጣሪነት በመጠቀም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፣ በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት ፣ በሚዲያ ዘርፍ እንዲሁም የኢትዮጵያን ቅርሶች በማስመለስ ዙሪያ በሚደረገው ጥረት ከኤምባሲው ጋር በቅርብ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግሯል ።
በቅርቡ በእንግሊዝኛ ያሳተመውን የልጆች ማሰተማሪያ መጽሀፍ ለአምባሳደር ተፈሪ መለስ ያስረከበ ሲሆን መጽሀፉ በዶክተር አሉላ ፓንክረስት በመተርጎም ለኢትዮጵያዊያን ልጆች ለንባብ እንደሚበቃ ገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።


( 232 Viewers) Back to Home

More News ..

"ከኢድ እስከ ኢድ" በሚል መሪ ቃል ወደ ሀገር እንግባ በሚል ለተላለፈው ጥሪ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳታፊ እንዲሆኑ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ጥሪ አቀረቡ Read More


ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የሹመት ደብዳቢያቸውን ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገቡ Read More


" ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አኩሪ ተግባር እንደሚፈጽሙ ዝነኛው ገጣሚ ለምን ሲሳይ ተምሳሌት ነው" ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነግጥም ሎሬት እና የማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ለምን ሲሳይ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከማልታ ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ Read More


ክቡር አምባሳደር አደም መሃመድ በቱርኮቹ አክሽ (AKIS) ፣ አክፋሊፍት ( AkFALIFT) እና በሌሎች ኩባንያንያዎች ጉብኝት አደረጉ Read More


ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን ጎብኝተዋል Read More


ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልምድ እና ተሞክሮ መቅሰም እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ክቡር ማዱት ቢያር ዬል ተናገሩ Read More


ዛሬ በተደረጉ በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1128 ዜጎች ተመለሱ Read More


ክቡር አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ የሹመት ደብዳቢያቸውን ቅጅ ለስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቀረቡ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ለማልታ ፕሬዝዳንት አቀረቡ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   1943
በዚህ ሳምንት:   48017
በዚህ ወር:   273733
በዚህ ዓመት:   1539771
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    4767369
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት