ክቡር አምባሳደር አደም መሃመድ በቱርኮቹ አክሽ (AKIS) ፣ አክፋሊፍት ( AkFALIFT) እና በሌሎች ኩባንያንያዎች ጉብኝት አደረጉ

(23-04-2022 published)
(ሚያዝያ 15 ቀን /2014ዓ/ም አዲስ አበባ ): በቱርክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አደም መሃመድ በኮኛ (Konya) ከተማ በመገኘት አክሽ ( AkIS) የሊፍት ሞተር አምራች እና እህት ኩባንያ ፍሌስ ካብ ( FLEX CAB) የኬብል አምራች የሆነ እንዲሁም አክፋሊፍት ኩባንያዎችን ጎብኝተዋል::
አክሽ በ1978 የተቋቋመ ፣ የቱርክን ከ82% በላይ ገበያ የሚሸፍን ፣ የሊፍት ሞተር በማምረት ከአለም እስከ አምስተኛ ደረጃ ፣ ከአውሮፓ ሁለተኛ ፣ ከቱርክ ደግሞ አንደኛ የሆነ ኩባንያ ነው::
በጉብኝቱም በአገራችን ያሉ የሊፍት ሞተሮች ጭምር ከዚህ ኩባንያ የተገኙ መሆኑን መረዳት ተችሏል::
ከዚህ በተጨማሪ በአክፋሊፍት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ኩባንያው የሊፍት ካቢን እና አውቶሜሽን ስራ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን ከ80 በላይ ሊፍቶችን ወደ ሀገራችን የላከ መሆኑን መረዳት ተችሏል::
አክፋሊፍት በሀገራችን ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚውል 50,000.00 የቱርክ ሊራ ለክቡር አምባሳደር አስረክቧል::( 672 Viewers) Back to Home

More News ..

"ከኢድ እስከ ኢድ" በሚል መሪ ቃል ወደ ሀገር እንግባ በሚል ለተላለፈው ጥሪ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳታፊ እንዲሆኑ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ጥሪ አቀረቡ Read More


ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የሹመት ደብዳቢያቸውን ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገቡ Read More


" ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አኩሪ ተግባር እንደሚፈጽሙ ዝነኛው ገጣሚ ለምን ሲሳይ ተምሳሌት ነው" ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነግጥም ሎሬት እና የማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ለምን ሲሳይ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከማልታ ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ Read More


ክቡር አምባሳደር አደም መሃመድ በቱርኮቹ አክሽ (AKIS) ፣ አክፋሊፍት ( AkFALIFT) እና በሌሎች ኩባንያንያዎች ጉብኝት አደረጉ Read More


ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን ጎብኝተዋል Read More


ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልምድ እና ተሞክሮ መቅሰም እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ክቡር ማዱት ቢያር ዬል ተናገሩ Read More


ዛሬ በተደረጉ በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1128 ዜጎች ተመለሱ Read More


ክቡር አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ የሹመት ደብዳቢያቸውን ቅጅ ለስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቀረቡ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ለማልታ ፕሬዝዳንት አቀረቡ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   9924
በዚህ ሳምንት:   67209
በዚህ ወር:   9924
በዚህ ዓመት:   1962405
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    5190003
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት