ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ለማልታ ፕሬዝዳንት አቀረቡ

(21-04-2022 published)
ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ተቀማጭነታቸውን በጣልያን ሮም አድረገው አገራችንን በማልታ እንዲወክሉ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሾሙበትን ደብዳቤ ቅጅ እ.ኤ.አ. አፕሪል 21 ቀን 2022 ለማልታ ፕሬዝዳንት ክቡር ጆርጅ ዊሊያም ቤላ አቀረቡ።
በእለቱ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሪዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለማልታ አቻቸው የተላከውን ሰላምታ አስተላልፈው በተሰጣቸው ሀላፊነት የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
ክብርት አምባሳደሯ አያይዘው ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በአገራችን እየተከናወኑ ስላሉ የልማት ስራዎች አብራርተዋል።
የማልታ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ጆርጅ ዊሊያም ቬላ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በአሁን ሰአት የተፈጠሩ ችግሮች እልባት እንደሚያገኙ ሙሉ እምነቱ እንዳላቸው ገልፀዋል።
አያይዘውም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ለዚህም በአገራችን በቅርቡ የማልታ ሪፐብሊክ ኤምባሲ መከፈቱ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይም ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በጋራ ለመስራት ፍላጎቱ እንዳላቸው ገልፀዋል።


( 186 Viewers) Back to Home

More News ..

"ከኢድ እስከ ኢድ" በሚል መሪ ቃል ወደ ሀገር እንግባ በሚል ለተላለፈው ጥሪ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳታፊ እንዲሆኑ ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ጥሪ አቀረቡ Read More


ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የሹመት ደብዳቢያቸውን ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገቡ Read More


" ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ አኩሪ ተግባር እንደሚፈጽሙ ዝነኛው ገጣሚ ለምን ሲሳይ ተምሳሌት ነው" ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስነግጥም ሎሬት እና የማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ለምን ሲሳይ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋና አቀረበ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከማልታ ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ Read More


ክቡር አምባሳደር አደም መሃመድ በቱርኮቹ አክሽ (AKIS) ፣ አክፋሊፍት ( AkFALIFT) እና በሌሎች ኩባንያንያዎች ጉብኝት አደረጉ Read More


ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን ጎብኝተዋል Read More


ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ልምድ እና ተሞክሮ መቅሰም እንደምትፈልግ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ክቡር ማዱት ቢያር ዬል ተናገሩ Read More


ዛሬ በተደረጉ በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1128 ዜጎች ተመለሱ Read More


ክቡር አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ የሹመት ደብዳቢያቸውን ቅጅ ለስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቀረቡ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ የሹመት ደብዳቤ ቅጅ ለማልታ ፕሬዝዳንት አቀረቡ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   10442
በዚህ ሳምንት:   67727
በዚህ ወር:   10442
በዚህ ዓመት:   1962923
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    5190521
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት