በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮን ቢሮ ተገኝተው ውይይት አደረጉ

(14-01-2021 published)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ጥር 06 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ክቡር ጃው ጂዩዋንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸው ከተነሱት ዋና ጉዳዮች መካከል የCOVID-19 ወረርሽኝ ፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ(GERD) እና ወቅታዊ የግራይ ክልል ሁኔታ፤ በተለይ በክልሉ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችን በሚመለከት ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል ፡፡
በውይይት ክቡር አቶ ደመቀ የጃክ ማ ፋውንዴሽንን ጨምሮ፣ የቻይና መንግስት እና ኩባንያዎች ዓለም አቀፉን ወረርሽኑን ለመዋጋት ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልፀዋል ፡፡
ቻይና ለኢትዮጵያ አንዳንድ ኘሮጀክቶች ለሰጠችው የብድር ፋይናንስ የኪፊያ ጊዜ ማራዘም እንደሚታደር ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመው፣ ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ላይ የወረርሽኙ የሚያስከትለውን አስከፊ ተጽዕኖ ለማቃለል የሚረዳ መሆኑንም አመልክተዋል ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በአፍሪካ ለሚፈጠሩ ችግሮች የአፍሪካ መፍትሄዎች” የሚለውን መርህ የሚያስተጋባውን ቻይናን በህዳሴ ግድብ / GERD / ድርድርን በተመለከተ የሚትከተለው በመርህ ላይ የተመሠረተን አቋም አድንቀዋል ፡፡
ክቡር አቶ ደመቀ በቅርቡ በትግራይ ክልል ስለተፈጠሩ ክስተቶች በሰጡት ማብራሪያ መንግስት በክልሉ የሕግ የበላይነትን ማስጠበቅ ዘመቻ አድርጎ በስኬት ማጠናቀቁን፣ ከዚያም በመቀጠል ከዓለምአቀፍ ምግባሬ ሴናይ ኤጀንሲዎች ጋር በሰብዓዊ ዕርዳታና በሌሎችም ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ ለማድረስ በጋራ ጥረት መቀጠሉን፣ እና በክልሉ የህወሃጽ ቡድን ያፈራረሳቸው መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ፡፡
የህወሃት መሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ እንዲሁም ክልሉ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን ክቡር አቶ ደመቀ አክለው ገልፀዋል ፡፡
አምባሳደር ጃው ጂዩዋን በበኩላቸው በCOVID-19 አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በአጋርነት በመቆሟ የመንግስታቸውን ምስጋና እና አድናቆት ገልፀዋል ፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ላደረጉላቸው ገለፃ ምስጋናቸውን ያቀረቡ አምባሳደሩ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ፡፡
በመጨረሻም ክቡር አቶ ደመቀ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የሚኖራቸው የሥራ ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን የኢትዮጵ መንግሥት የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ቃል ገብተውላቸዋል።


( 87 Viewers) Back to Home

More News ..

የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዓውደ-ጥናት በአዲስ አበባ ተካሄደ Read More


በኔዘርላንስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዌብናር አካሄደ Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞሐመድ አብዲራዛቅን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ Read More


የኬንያው ፕሬዝዳንት የዶ/ር አብይን መልዕክት ተቀበሉ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአሜሪካ አምባሳደርን ተቀብለው አነጋገሩ Read More


ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ለአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ግንኙነትና ልማት የጋራ ኮሚቴ አባላት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና የሹመት ደብዳቤ ቅጂ ተቀበሉ Read More


ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ዜጎች ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   678
በዚህ ሳምንት:   42290
በዚህ ወር:   13463
በዚህ ዓመት:   388496
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    1230465
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት