የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ሻልለንበርግን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ

(14-01-2021 published)
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አሌክሳንደር ሻልለንበርግ ጋር በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ እና በክፍለ-ዓለሙ የተከናወኑ ጉዳዮችን ዙሪ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
ክቡር አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ እና ኦስትሪያ ለዘመናት የዘለቀ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ አገራት መሆናቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ሀገሮች መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ሲናገሩ፣ በትግራይ ክልል የተካሄደው ሕግን የማስከበር እርምጃ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን፣ በክልሉ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይ የሰብዓዊ ዕርዳታ በወቅቱ መድረሱን ለማረጋገጥ፣ የመልሶ ግንባታና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ አሰጣጥ ላይ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ከመንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
ክቡር አቶ ደመቀ አክለው በኢትዮጵያ የለውጥ ኃይል የሚመራ መንግሥት በአዲስ መልክ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ቀጣይነጽ ያለ ሰላምና ልማት በክፍለ- አህጉሩ እንዲረጋገጥ ለተመዘገቡ አወንታዊ ለውጦች ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉን አስምረውበት በዝርዝር አስረድተዋል ፡፡
የኦስትሪው ጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሚስተር ሻልለንበርግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው ቁልፍ ሚና የምትጫወት ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ሀገር መሆኗን እና ለኦስትሪያ የልማት ትብብር መርሃ ግብር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ሀገሮች አንዷ በመሆኗ፤ የተጀመሩ የልማት ጥረቶችን ለመቀጠል አገራቸው ቁርጠኛ እንደሆነች ተናግረዋል ፡፡
ሚስተር ሻልለንበርግ የሰብአዊ ዕርዳታ ለተቸገሩ ወገኖች እንዲደርስ ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት መቀጠል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው፣ ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል ፡፡
ክቡራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ባደረጉት ውይይት የሰብአዊ ዕርዳታ ሥራ እና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የሚደረገው ርብርብ ማጠናከር አስፈላጊነት ላይ ከመግባባት ደርሰዋል። እንዲሁም በሁለቱ እህትማማች አገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ትብብርን በማጎልበት በጋራ መስራታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል ፡፡


( 101 Viewers) Back to Home

More News ..

የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዓውደ-ጥናት በአዲስ አበባ ተካሄደ Read More


በኔዘርላንስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዌብናር አካሄደ Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞሐመድ አብዲራዛቅን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ Read More


የኬንያው ፕሬዝዳንት የዶ/ር አብይን መልዕክት ተቀበሉ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአሜሪካ አምባሳደርን ተቀብለው አነጋገሩ Read More


ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ለአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ግንኙነትና ልማት የጋራ ኮሚቴ አባላት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና የሹመት ደብዳቤ ቅጂ ተቀበሉ Read More


ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ዜጎች ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   736
በዚህ ሳምንት:   42348
በዚህ ወር:   13521
በዚህ ዓመት:   388554
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    1230523
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት