የኢትዮጵያ ባህላዊ እሴቶች እና ትውፊቶች በቤተ እስራኤል ማኅበረስብ በሚል ርዕሰ የበይነ መረብ ዐውደ ጥናት ተካሂደ።

(12-01-2021 published)
የኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ በእስራኤል ከኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር እና ከእስራኤል የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የበይነ መረብ ዓውደ ጥናት ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ተካሄዷል። ዐውደ ጥናቱ “ኢትዮጵያዊ እሴቶች እና ባህላዊ ትውፊቶች በቤተ እስራኤል ማህበረሰብ ከትናንት እስከ ዛሬ” በሚል ርእስ የተደረገ ሲሆን በመርሀ ግብሩ አራት ትውልደ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊያን ምሁራን ጥናታቸውን አቅርበዋል።
በዚህ መርሀ ግብር በእስራኤል ክቡር አምባሳደር ረታ ዓለሙ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
አምባሳደር ረታ በንግግራቸው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በዳያስፖራ ዘርፍ አንዱ ትኩረቱ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከአገራቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት ማጠናከር መሆኑ ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ ባህላዊ እሴቶችና ትውፊቶች፣ ምግቦቻችን፣ ልብሶቻችን፣ ዘፈኖቻችን በሌላው ዓለም ማህበረሰብ ዘንድ አድናቆትን ያተረፉ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ቤተ እስራኤላዊያን ኩሩ፣ ጠንካራና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለማፍራት የራሱን እሴትና ባህላዊ ትውፊት አለባበስ፣ አመጋገብ፣ ቋንቋዎች፣ ኪነጥበብ፣ የመሳስሉትን ሀብቶች ጠብቆ የሚያቆይ ትውልድ ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል።
ከዚህ አንጻር በማኅበረስቡ አባላት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን እና ኢምባሲያችን በእስራኤል ይህንን የቤተ እስራኤላዊያን ጥረት ለመደገፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በማያያዝም “በእስራኤል የምትኖሩ ወገኖቻችን የሁለቱን አገሮች ወዳጅነትና ትብብር ለማጠናከር ከምታደርጉት ጥረት አንጻር በባህል ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ትልቅ ሚና አላችሁ።” በማለት ለማህበረሰቡ አባላት ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ረገድ በጋራ በመስራት ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ለመገንባት ልንቀሳቀስ ይገባል” ብለዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ባደረጉት ንግግር ቤተ እስራኤላዊያን ለሦስት ሺህ ዓመታት የዘለቀ ትስስር መሰረት መሆናቸውን እንደዚሁም ማህበረሰቡ ባህል እና ቋንቋውን ጠብቆ ለልጅ ልጆቻቸው ለማሸጋገር የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፤ መንግስት በኢትዮጵያ የነበሩትን ታሪካዊ ሥፍራዎች በማልማት፣ ቅርሶቻቸውን በማሰባሰብ፣ የባህል ማዕከላትን እና ሙዚየሞችን በመገንባት መጪው ትውልድ ባህላዊ እሴቱን እና ትውፊቱን ጠብቆ እንዲቆይ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በማያያዝም ቤተ እስራኤላዊያን በሀገር ቤት የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል፤ በተለይም ወጣቱ ከትውልድ ሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር እና ተሳትፎውን ለማሳደግ እንዲችል የትውልደ ኢትዮጳያ ካርድን ጨምሮ በመንግስት የተለያዩ አሰራሮች መዘርጋታቸውን ገልጸዋል።
በዐውደ ጥናቱ ዶ/ር ንግስት መንገሻ ”ባህላዊ እሴቶች እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ፋይዳ” በሚል ርዕስ ጥናታቸውን አቅርበዋል።
ዶ/ር መልካሙ ያዕቆብ “ሲወርድ ሲወራረዱ ለመጡት ባህላዊ እሴቶች እና ባህላዊ ቅርሶች በትውልዶች ሂደት” የሚደረገው ቅብብሎሽ በሚለው ርዕስ ገለጻ ሰጥተዋል። በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር አንበሴ ተፈራ “ቋንቋ ከባህላዊ እሴቶች ጋር ያለው ቁርኝት” በሚል ርዕስ ስር ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እንዲሁም በእስራኤል በሚገኘው የኦኖ አካዳሚክ ኮሌጅ ከፍተኛ መምህር እና የኢትዮጵያ አይሁዳዊያን ጥናት ዓለም አቀፍ ማዕከል ኃላፊ በሆኑት ራቪ ዶ/ር ሻሮን “የእሴቶች አጠባበቅ በኅብረ ባህላዊ አውድ ውስጥ” በሚል ርዕስ ስር ገለፃ ቀርቧል።
መድረኩን የመሩት ታዋቂው ጋዜጠኛ አቶ ራህሚም አላዛር ናቸው፤ ከገለጻውና ከጥያቄና መልስ በተነሱት ነጥቦች አምባሳደር ረታ እና ወይዘሮ ሰላማዊት የማጠቃለያ አስተያየት ሰጥተዋል።
ይህ ዐውደ ጥናት ኢምባሲው በሁለቱ ሀገራት መሀከል በባህል ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደዚሁም ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከአገራቸው ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጠናከር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሀ ግብሮች የመጀመሪያው ክፍል ነው። በቀጣይ ከወጣቶች ጋር በመሆን ተመሳሳይ ዝግጅቶች የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።( 94 Viewers) Back to Home

More News ..

የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዓውደ-ጥናት በአዲስ አበባ ተካሄደ Read More


በኔዘርላንስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዌብናር አካሄደ Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞሐመድ አብዲራዛቅን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ Read More


የኬንያው ፕሬዝዳንት የዶ/ር አብይን መልዕክት ተቀበሉ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአሜሪካ አምባሳደርን ተቀብለው አነጋገሩ Read More


ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ Read More


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ለአውሮፓ ፓርላማ የውጭ ግንኙነትና ልማት የጋራ ኮሚቴ አባላት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ Read More


ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና የሹመት ደብዳቤ ቅጂ ተቀበሉ Read More


ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ዜጎች ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ Read More


Read More News...

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   731
በዚህ ሳምንት:   42343
በዚህ ወር:   13516
በዚህ ዓመት:   388549
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    1230518
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት