የውጭ ኢንቨስተሮችን የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የተቋቋመ የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

(05-01-2021 published)
ዛሬ ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እና የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው የውጭ ኢንቨስተሮችን የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የተቋቋው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።
በስብሰባው የቅንጅት መደረኩ አስፈላጊነት፣ የውጭ ባለሀብቶች በአገራችን እያደረጉ ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎች፣ የማነቆዎቹ አፈታት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በስብሰባው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክብርት ሌሊሴ ነሜ የድህረ ኢንቨስትመንት ክትትል በተመለከተ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ላይም ውይይት ተደርጓል።
በጽሁፍም በአገር ውስጥ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ባለሃብቶች ማቆየት፣ ማስፋፋትና ትስስር መፍጠር የሚችሉበትን (retention, expansion and linkage) አንጻር በአገራችን የኢንቨስትመንት ነበራዊ ሁኔታ የሴክተር መ/ቤቶች የራሳቸውን ተቋም ብቻ ትኩረት ማድረግና የመቀናጀት ውስንነት መኖሩ፣ የኢንቨስትመንት መመሪያ የመረዳትና ባለሃብቶችን የመቀበል (welcome) ችግሮች መኖሩ እንዲሁም፣ የኮቪድ-19 ተጽዕኖ በቀጥተኛ ኢንቨስት/FDI/ ፍሰት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ መፍጠሩም በኮሚሽነሯ ገለፃ ከተዳሰሱ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡
በመጨረሻም ውይይቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የቅንጅት መድረኩ የጋራ ተግባራት በማጠናከር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በስፋት መሳብ እንደሚያስፈልግና በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል። በስብስባው ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች የመጡ ሚኒስትሮች እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


( 360 Viewers) Back to Home

More News ..

Ambassador Hirut Zemene confers with Member of the #European Parliament Chrysoula Zacharopoulou Read More


Deputy Prime Minister and Foreign Minister of #Ethiopia Demeke Mekonnen welcomes #Austrian Foreign Minister Alexander Schallenberg Read More


#Chinese ambassador to #Ethiopia pays a courtesy call on Deputy Prime minister and Foreign Minister Demeke Mekonnen Read More


Ambassador Yibeltal Aemero Underscores the Need for Peaceful Resolution of the Differences Regarding the #Ethiopia- #Sudan Boundary Read More


Ambassador Deriba Kuma meets members of the #Swedish parliament (#Riksdag) Read More


#Ethiopian Embassy facilitates repatriation of 179 trucks of Trans Ethiopia parked illegally in #Djibouti Read More


Ambassador Hirut Zemene confers with #Belgian Import -Export Agency representative on investment opportunities in Ethiopia Read More


#Ethiopia/n mission in #France holds Successful Coffee Promotion Webinar Read More


Ambassador Samia Zekaria confers with #Sudan ambassador in Qatar Read More


High-level e-workshop on Environmental Diplomacy Kicks off today Read More


Read More News...

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   5435
THIS WEEK:   33336
THIS MONTH:   106660
THIS YEAR:   106660
TOTAL:    948629
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Regions
      * Neighboring Countries
      * African Countries
      * Middle East Countries
      * Asia Countries
      * Europe Countries
      * United State of America
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts