የሰው ዘር መገኛ ኢትዮጵያ፡
የሰው ዘር አመጣጥ በኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አብዛኛውን የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ትሸፍናለች። የቅሪተ አካል ምርምር ማስረጃዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ ከ Chororapithecus Abyssinicus ( 12-7 ሚሊዮን አመት በፊት የተገኘው ሰው መሳይ ጦጣ) ጀምሮ እስከ homo sapiens(ብልቱ ሰው) እየተባለ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን ትሸፍናለች። ይህም ማለት በአፋር ክልል ሆርቶ አካባቢ ከ 160,000 እድሜ እስካለው የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ ሂደት ማለት ነው።
በቅርቡ ከተገኙ ግኝቶች ደግሞ 4.4 ሚሊዮን አመት ያለው Ardipithecus kadaba እና ከ 3.3 ሚሊዮን አመት በፊት ኑራለች ተብሎ የሚገመተው የተሟላ ሰውነት ያላት ሰላም ይገኙባታል። በቅሪጸ አካል ግኝት በጣም ታዋቂ ሆነችውና ከተሟላ የሰውነት አካላ ጋር የተገኘችው ሉሲ በሳየንሳዊ አጠራሯ "Australopithecus Afarensis" ወይም ድንቅነሽ የሚል መጠሪያ የተሰጣት ከ3.2 ሚሊዮን አመት በፊት ጥኖር የነበረችውና በጊዜው በሁለት እግሮቿ መንቀሳቀስ የቻለች የሶስት ጫማ ርዝመት ያላት ናት።
ሉሲ የተገኘችው በአፋር ክልል ሃዳር በሚባል አካባቢ ነው። በአሁኑ ወቅት የሉሲን ምስል የያዘው ቅሪተ አካል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም ውስጥ ለሁሉም ጎብኚዎች ክፍት ሁኖ ይገኛል። በአጠቃላይ የሰው ልጅ ዝግመተ ለውጥ የሚጀምረው ከ Australopithecus ሲሆን በሂደትም ወደ ተቀየረ፡፡ Genus homo ሶስት የለውጥ ሂደቶች አሉት በቅደም ተከተልም እንዲህ እናስቀምጣቸዋለን።

  1.  Homo habilse (2.4-1.8 ሚሊዮን አመት) 
  2. Homo erects ( ከ 1.4-1 ሚሊዮን አመት) 
  3. Homo sapiens (ከ200,000 አመት በፊት)Back to Home

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   781
በዚህ ሳምንት:   42393
በዚህ ወር:   13566
በዚህ ዓመት:   388599
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    1230568
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት