የመንግሥት አወቃቀር
ኢትዮጵያ በመድበለ ፓርቲ ስርዓት፣ በሕግ አውጪው አካል እና በሕግ አስፈፃሚው ጠ/ሚኒስቴር የበላይነት በተመረጡ የተወካዮች ም/ቤት /547 አባላት/ እና የፌዴሬሽን ም/ቤት /110 አባላት/ የምትመራ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ናት ፡፡
በየ 5 ዓመቱ የሚካሄደውን ዲሞክራሲያዊ መድብለ ፓርቲ ስርዓት የተከተለ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን በመጠበቅ ጠ/ሚኒስትሩ በሥልጣን ላይ ባለው ፓርቲ ይመረጣል፡፡ እንዲሁም ፕሬዝዳንቱ በተወካዮች ም/ቤት አባላት ይመረጣል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሄራዊ ወይም በፌዴራል ደረጃ ይመዘገባሉ፡፡
ፕሬዝዳንት፡ ክብርት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ
ጠ/ሚኒስትር፡ ክቡር አቶ አብይ አህመድ(ዶ/ር)
የተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ፡ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ ካቢኔ /ጥቅምት 2011/
1. ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የሰላም ሚኒስትር
3. ክቡር አቶ ቀነዓ ያደታ(ዶ/ር) - የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
4. ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
5. ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር
6. ክቡር አቶ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) - የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
7. ክቡር አቶ ኡመር ሁሴን - የግብርና ሚኒስትር
8. ክቡር አቶ መላኩ አለበል - የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
9. ክቡር አቶ አብርሐም በላይ(ዶ/ር) - የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
10. ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ - የትራንስፖርት ሚኒስትር
11. ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር
12. ክቡር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር) - የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
13. ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ - የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር
14. ክቡር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
15. ክቡር አቶ ሳሙኤል ሁርካቶ(ዶ/ር) - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
16. ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ - የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
17. ክብርት ወ/ሮ ፊልሳን አብዱላሂ - የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር
18. ክብርት ወ/ሮ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) - የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. ዶ/ር ሂሩት ካሳው - የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
20. ክቡር አቶ ላቀ አያሌው - የገቢዎች ሚኒስትር
21. ክብርት ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) - የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር