በዓላማችን ሞቃት ቦታዎች በጣም ዝቅተኛው ወይም ወደታች ዝቅ ብሎ የሚገኝ ነው፡፡
አፍሮ አልፓይን የሚባሉ የከፍታ ቦታዎች፣ ቁጥቋጦዎች፣ ተራራዎች፣ ጥልቅ ገደልማ የወንዝ ሸለቆዎች፣ የሶፍ አመር ዋሻ (በአፍሪካ ሰፊው ነው) ታላቁ ስምጥ ሸለቆ እና ሐይቆች፣ የሰሩር አውራጃ ዝናባማ ጥቅጥቅ ደኖች፣ የፏፏቴ ወንዞች፣ የሳር መሬት ምድር፣ የእሳተ-ገሞራ ፍል ውሀዎችና እሳተ ገሞራዎች እኚህ ሁሉ በደበረ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ አርኪዮሎጂያዊ እና የስነ ባህል (Anthropology) ቦታዎች የታገዙ ናቸው የሰሜኑ "ታሪካዊ ጎዳና" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ ዋና ከተማ ጎንደር (17 18 ክፍለ ዘመን) አክሱም ደግሞ (1 እስከ 8 ክፍለ ዘመን) እና ላሊበላ (12 እስከ 13 ክፍለ ዘመን) ከውቅር አቢያተ ክርስቲያናቱ ጋር እንዲሁም ጣና ሀይቅ ላይ ያሉት ገደማት (የዓባይ ወንዝ ፏፏቴ) ብዛት ያላቸው የትግራይ ክልል የዕለት ቤተ-ክርስቲያኖች አብዛኞቹ 14ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ከዚያም በፊት ናቸው፡፡ 

 ዋነ ከተማዋ አዲስ አበባ 2005 . 125 ዓመቷን አክብራለች 1879 በአፄ ሚኒሊክ የተመሰረተችው አዲስ አበባ ታሪኩ እንደሚያስረዳው በእንጦጦ ተራራ ላይ ቤተ-መንግስት ከወደፊቷ አዲስ አበባ አንድ ሺህ ሜትር ከፍ ብሎ ተቆረቆረች፡፡ ንግስቲቱ ጣይቱ የተራራውን ጫፍ በጣም ቀዝቃዛና ዕርጥበታማ ሆኖ አገኙትና ከጋራው ግርኔ ወዳሉት ፍል ውሀዎች ተጠጉና ላለመመለስ ወሰኑ፡፡ አፄ ሚኒሊክ ሁለት ዓመት ንግስቲቱን ጣይቱን ከጠበቁ በኋላ ባለቤታቸውን ለማየት ያላቸው አማራጭ ቤተ-መንግስታቸውን ንግስቲቱ ካሉበት ቅድስት ማርያም ሙዝየም የሚባል ንግሱ መጀመሪያ ከሰፈሩባቸው ቦታ ላይ ተቋቋማል፡፡ ታሪካዊ መዛግብት፣ ንጉሳዊ ዘውዶች፣ የተለያዩ የንጉስና የንግቲቱ የክብረ በዓል አልባሳትና 1989 ጣሊያን በተሸነፈበት የአድዋ ጦርነት የተጎሰሙ ነጋሪቶች ይገኙበታል፡፡ 

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዝየም የጥንት ድንቅነሽ የቅድመ ሰብ ቆሪቶችን (3.4 ሚሊዮን አመት ያስቆጠረች) እና ሪሚደስ (4.4 ሚሊዮን ዓመት) እንዲሁም ጌጣ ጌጦች፣ አልባሳት ስእሎች እና ቅርፃ ቅርጾች ይዞ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ጥናቶች ኢኒስቲቲዩት በቀድሞ የአጼ ሐይለ ስላሴ ቤተ መንግስት አሁን ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አካል የሆነው የብሄሮች ሙዝየም ይገኛል፡፡ 

 

የእንስሳት ተፈጥሯዊ ታሪካ ሙዝየም የኢትዮጵያን የዱር እንሰሳት ሀብት የሀገሪቷን ርቅዬ በሌሎች አለማት የማይገኙ ዝርያዎች እንደ ረዛም ያለ የፊት ጥርስ ያላቸው አጥቢ አንስሳት ለአብነት አይጥ፣ የለሊት ወፎች፣ ስጋ በል እንስሳት፣ ቀደምት ዛፍ ላይ የሚኖሩና የዝንጀሮና የሰው ልጅ ዝርያዎች አዋፋት፣ የእባብ ዝርያዎች፣ የእንሽላሊት ዝርያዎች፣ በየብስና በውሀ የሚኖሩ ፍጡራን፣ አሳዎችና የጀርባ አጥንት አልባ እንሰሳት። በመዲናዋ አዲስ አበባ ጥቂት የማይባሉ የቤተ ዕምነት ሙዝየሞችም ቀልብ ከሚገዙ ስዕሎች ጋር ይገኛሉ፡፡ 

የኢትዮጵያ የፓስታ ሙዝየም የተለያዩ የሀገሩቱን ቴምብሮች ይዞ ይገኛል፣ የአዲስ አበባ ሙዚየም በቀድሞ የራስ ብሩ ቤተ-መንግስት 19ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ የተገነባው የከተማዋና የእድገት ሂደት የሚያሳዪ ፎቶ ግራቾች አሉትና እዛው ቅርብ የሚገኘው የቀይ ሽብር ሙዝየም የቀይ ሽብርን 1967-70 የተለያዩ አጥፊ ተግባራትን ያሳያል፡፡ ከተማይቱ የተለያየ መናፈሻ ፓርኮች አሏት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አጠገብ የሚገኘው የአንበሳ ፓርክ እየጠፋ የመጡትን ጥቁር ጋማ ያላቸው አንበሶችን ይዞ ይገኛል፡፡ 

 

የአለም የቅርስ መገኛ ኢትዮጵያ በአሁኑ ግዜ ዘጠኝ የዩኔስኮ (UNESCO) የተመዘገቡ የዓለም የቅርስ ቦታዎች አሏት ከሁሉም በቅርብ ግዜ የተመዘገበው የኮንሶ ባህላዊ መልክአምድር ነው፡፡ 55 ስክዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የድንጋይ ድርድር የተሰራ ግድግዳና በድንጋይ የጠነከሩ በኮንሶ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የኮንሶ ቤቶች፡፡ እኚህ ቅርሶች በብዙ ሺህ ሰዎች የሚጎበኝ 21 ትውልዶች ወደ ኋላ ድረስ የነበሩ የባህል ቱሩፋቶች ናቸው (400 ዓመታት በላይ) በአብዛኛው ደረቅና አደጋ የበዛበት አካባቢ የኖሩ ትውልዶች ናቸው፡፡ 

 

የዚህ መኖሪያ ስፍራ ባህርያት ለአብነት ሰው መሰል የእንጨት ቅርፆች የማህበረሰቡን አባላት ለመግደልና የጀግንነት ሁኔቶችን ለማሳየት የሚጠቀሙት፣ ሊጠፋ የተቃረቡ የቀብር ስነ ስርዓት፣ የሚያሳዩ ውስብስብ ስርዓት የሚገልፁ ናቸው፡፡ በሶዶ አካባቢ መቶ ስልሳ የአርኪዮሎጂ ቦታዎች የተገኙ ሲሆን ጥያ ከዋናዎቹ አንዱ ነው የሶዶ አካባቢ ከአዲስ አበባ ደቡባዊ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ታሪካዊ ቦታው 36 ሐውልቶች፣ 32 ከአለት የተቀረፁ የተለያዩ ምልክቶች ያሏቸው ትክክል ድንጋዮችን አብዛኞቹ ወደ ቀላል ቋንቋ ለመቀየር ከባድ የሆኑትን አካቶ ይዟል፡፡ 

 

እነዚህ የአለት ትክል ድንጋዮች የኢትዮጵያ የጥንት የባህል ቅሪቶች ሲሆን እስካሁን ዕድሜያቸው በውል ያልታወቀና የየትኛው ዕድሜ ስንት እንደ በግልጽ ያስቀመጠ ነው፡፡ ሰሜን ብሄራዊ ፓርክ ታልቅ ጎርፍ በኢትዮጽያ ሜዳማ ቦታዎች ላይ ተከስቶ የነበረው ጎርፍ ጥልቅ ሸለቆዎችና እስከ 1500 ሜትር ድረስ የሚወርዱ ጥልቅ ገደሎች ያለውን መልካአ ምድ ፈጥሯል፡፡ (Listed in 1978) ብሄራዊ ፓርኮች አዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ከሀገሪቷ የዱር አራዊት ጥብቅ ፓርኮች ዕድሜ ጠገቡ ነው፡፡ የፈንታሌ እሳተ-ገሞራን፣ ብዛት ያላቸው የተፈጥሮ ፍል ውሀዎችና ልዩ የእሳተ ገሞራ ተፈጥሮ ዉጤቶች እንዲሁም የአዋሽ ወንዝ በተለይ ቀልብ የሚገዙ የወንዙ ፏፏቴዎች ከሶስት ሰዓት ባነሰ የመኪና ጉዞ ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ሁለት መቶ ሀያ አምስት ኪሎ ሜተር ይሆናል ከመዲናዋ አዲስ አበባ፡፡ 720 ኪሎ ማትር ስኩዌር በሚሸፍነው ቦታው ላይ ሚዳቋ፣ ዋልያ፣ ድኩላ፣ የሜዳ አህያ፣ አቦ ሸማኔ፣ አነር፣ የጭላዳ ዝንጀሮና አረጓንሬ ዝንጀሮዎች፣ ትልልቅ ኤሊዎች፣ ጉማሬ እና የተለያዩ የዱር እንሰሳት አሉ፡፡ ከአራት መቶ በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች በፓርኩ ተመዝግበዋል፡፡ ከሰጎን አንስቶ እስከ አቢሲኒያን ግራውንድ ሆርንቢል፣ ከቀይዋ ንብ በል ወፍና አቢሲያን ሮለር እስከ ኩኩና የተለያ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡

 

የባሌ ተራራዎች ፓርክ በከፍተኛ ቦታዎች ሜዳ ላይ ያለ ሲሆን በእሳተ ገሞራዎች ፍንዳታዎች ምክንያት የተፈጠሩ የተራራ ጫፎች ያሉት የአልፓይን ሀይቆች እና የተራራ ዕንፍሎች ያሉት ድንቅ ቦታ ነው፡፡ 

ከሜዳማው ቦታ በርካታ የተራራ ጫፎች ይነሳሉ ቱሉ ዲምቱ ጨምሮ 4.377 ሜትር ሁለተኛው ነው፡፡ በአፍሪካ ትልቁ የአፍሮ አልፓይን መኖሪያ ሥፍራ ነው ይህ ተራራ እና ያልተዳሰሰ የተራራ ሪምጂ እድል ይሰጣል፣ የፈረስ ጉዞ፣ የመኪና ጉዞና የኢትዮጵያን ብርቅየየ አጥቢ እንሰሳት ለማየት እድል ይሰጣል፡፡ 

 

በዋነኛነት የተራራ ንያላ የሚኒሊክ ድኩላና ቀፋ ቀበሮ ይገኙበታል፡፡ ብርቅዬ አዕዋፍ ደግሞ ሪቨን፣ ዋትልድ ኢቢስ፣ ብሉ ዊንግድ ጉዝና ሩጄኑስ ረይል፡፡ ሌሎች የአዕዋፍ ዘርያዎች ደግሞ ጥቁር ክንፍ ያላት የፋቅር ወፍና ቢጫ ጫፍ ያለው በቀን፣ አኢሲኒያን ካትቦርድ፣ አቢሲኒያን ሌንግክላው፣ ብላክ ሄድድ ሲስከን፣ ሩዲያ ሼልደክ፣ ዋትልድ ክሬን፣ ለሜርዥርና ብላክ ሄድድ ሲስከን፣ ረድያ ሼልደክ፣ ዋትልድ ክሬን፣ ለሜርዥርና ጭልፊት ያገኙበታል ፡፡Back to Home

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   10806
በዚህ ሳምንት:   68091
በዚህ ወር:   10806
በዚህ ዓመት:   1963287
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    5190885
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት