የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች እንደመሆኗ መጠን .. 1963 ኢትዮጽያ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት አላማዎች መሳካት ታግላለች፡፡ በቅኝ ግዛት ወቅት የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን እንዲያገኙ በድብቅም ሆነ በገሀድ ታግላለች፡፡ ባለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት ከዚህ በፊት የነበረው ሀገራዊ ፓሊሲ ውጤታማ ባልሆነ ግዜ እንኳ ለአፍሪካ ተይዘው የነበሩት ፓሊሲዎችና ተግባራት የላቁ ነበሩ፡፡ ሀገሪቷ አህጉራዊ ሀላፊነቱን እንድትወጣና በምላሹም አፍሪካዊ ወንድሞችንና እህቶች ክብርን አስገኝቶላታል፡፡

ኢትዮጵያ ብቻዋን በነበረችበት ግዜ እንኳ የአፍሪካንና የአፍሪካውያንና ጉዳይ በሚያወላዳ መልኩ አጠንክራ የያዘች ሀገር ነበረች፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ከአፍሪካዊ ሀላፊነታቸው ራሳቸውን ገሸሽ ያደረጉበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፡፡ኢትዮጵያ የአፍሪካን ፓለቲካዊም ሆነ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ፈልጋ የተነፈገችበት ግዜም የለም፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለጥቆ የተመሠረተው የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ኢትዮፕያ ናት፡፡ ይህ ማለት የውጭ ጉዳይና የብሄራዊ ደህንነት ፓሊሲ እና ስትራቴጂ እንደሚጠቅመው ኢትዮጵያ የህብረቱን ልዩ ሀላፊነት ተሸክማለች፡፡ በርግጥም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ያለውን የተሳሰረች፣ የበለፀገችና ሠላማዊ ብሎም ከግዜው ጋር የሚለዋወጥ ሀያልን በአለም አቀፍ መድረክ እንድታቀርብና እንድትወክል ያለውን ራዕይ ትደግፋለች፡፡

ይህንን አፍሪካዊ ራዕይ ለማሳካት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሣታፊ ከመሆኗም ባሻገር አፍሪካን ለዘመናት ቁም ስቅሏን ሲያሳያት የነበሩትን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከመፍታት ጥረቷ ዞር እንኳ ብላ አታውቅም፡፡

እያደገች ያለች የአፍሪካ የብዙ ቋንቋና ባህል ማዕከል

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ዛፎች መሀል ለመሀል የተደረደሩባቸው ሰፋፊ መንገዶች፣ ድንቅ የስነ-ህንፃ ጥበቧ፣ ተስማሚ የአየር ሁኔታና አውራጎዳናዎቿን በሰልፍ የሚጓዙበት የአህያ ጋሪዎች አዲስ አበባን ለጉብኝት ተመራጭ ያደርጋታል፡፡

አዲስ አበባ መዲናችን በልዩነት፣ በግርምትና በብዛህነት የተሞላች ከተማ ናት፡፡ የባህር ዛፎች፣ ነፋሻማ አየር፣ ንፁህ የተራራ አየር አዲስ አበባን በከፍታ ቦታዎች ተስማሚ የአየር ንብረት አድሏታል፡፡ ምቹ የኤስፔሬሶና ቡና ቤቶች፣ ኬክ ቤቶቿ ሮምን ሜዴቴሬንያንና የደጂ ለይ ገበያዎቿ ደግሞ ባህላዊ ኑሮን የሚያሳዩ ደማቅ ምስል ናቸው፡፡ ህዝቦቿ፣ ከየሙዚቃ ቤቶች ካፌዎችና ሱቆች የሚወጣው ድምጽ፣ የጣፍጭ ምግቦች የቡና ሽታ፣ እጦን ሲጨከለየት ያለ ኢትዮጵያዊ እንዲሁም ቅልቅል ማዕዛ አለው፡፡

አዲስ አበባ እንደማንኛውም የዓለም ከተማ ሁሉ የተለያዩ የባህል የአለመካከት የኋላ ታሪክ ያላቸው ህዝቦች ያሉበት ትልቅ ከተማ ናት፡፡ እናም ስነ-ህንፃዋም እንደ ከተማው ሁሉ ብዛህነት የሚታይበት ነው፡፡ ረጃጅም ኦፊሴላዊ ህንፃዎች፣ ግርማ ሞገስ ያላቸው ሺላዎች፣ ለተለያዩ ዓለማዎች የተሠሩ ቤቶች፣ ሰርቪስ ቤቶች፣ ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የስብስባ አደራሾች እና በዕምነ-በረድ አሉሚኒያም ያጌጡ ትያትር ቤቶች፣ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ የሚመስሉ ባህላዊ የጫቃ ቤቶች፣ በከብቶች፣ በፍየሎች፣ በበጎች በዶሮዎች ተከበው ይገኛሉ፡፡

በአዲስ አበባ መሀል ከተማ ተብሎ በውል የተቀመጠ ቦታ የለም ምክኒያቱም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የከተማ ፕላን አልነበረም አዲስ አበባ በተፈጥሯዊና ጤናማ ዕድገት ነው ያደገችው እናም አሁን የሚታየው ገጽታዋ ሰው ሰራሽ ዕድገት ወይም ለውጥ እንዳልነበራት ያሳያል፡፡ ከፍታው እየጨመረ ከሚመጣው ገጠር 2300 እስከ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ከተመሰረተች አንድ ክፍለ ዘመን የበለጠ ጊዜ ያልሆናት አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ትልቋ ከተማ በሚያስደምም ሁኔታ አድጋለች፡፡

250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የምትሸፍነው ይህች ከተማ በዛፎች በተሸፈኑ ጋራዎችና እና በወንዞች ፍሰት በተፈጠሩ ሸለቆዎች መሀል ለመሀል ተንሠራፍታ ትገኛለች፡፡ ምንም እንኳ ለምድር ወገብ ቅርብ ብትሆንም አዲስ አበባ ከፍታዋ በዓለም ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጣት አየር ንብረቷ መካከለኛ ማለትም የሙቀት መጠኗ በአሸሬጂ 16oc (61of) በአብዛኛው ሞቃትና ደረቅ የሚባሉት ወራት ሚያዝያና ግንቦት ሲሆኑ በነዚህ ወራት ቀን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ ሞቃት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ ነፍሻማ ነው፡፡ በዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ ቀናትም ማታ ቀዝቃዝ ያሉ ናቸው፡፡ ከጥቅምት እስከ ጥር አጋማሽ የማታዎች አየር ሁኔታ እስከ (40) ይቀዘቅዛል ነገር ግን ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ክረምት ወቅት የሚመጡ ጎብኚዎች የአዲስ አበባን አየር ንብረት እጅጉን ተስማሚ ሆኖ ያገኙታል።፡

 

የአለም አቀፍ ኮንፈረንሶችና ሁኔታዎች አዘጋጅ

ኢትዮጵያ የተለያየ ህጎችን የሚያዘጋጁ፣ በሀገራት እርስ በእርስ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ፣  አለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን የሚገዙ ህጎች እንዲከበሩ የሚሰሩ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መስራች አባል ናት፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትብብርን በሀገራት መካከል ለማጠናከር የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ጽኑ ዕምነት አላት፡፡

እነዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባዘጋጁት መድረክ መሠረት ኢትዮጵያ ህጉን ተከትላ በዚህ በግሎባላይዜሽን ዘመን የበኩሏኝ እየተወጣች ነው የምትገኘው፡፡

ስለዚህም ነው እንግዲህ ኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያሉ ሀገሮች የዓለም አቀፍ ጨዋታን ህጎችና የሌሎችን ጥቅም ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለባት የምታምነው፡፡ የሚትዮጵያ ሚና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥም ሆነ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ያላት ትብብር አንዱ ታላቁ የሀገሪቷ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያላት ተሣትፎ አካል ነው፡፡

የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ማለቁን ተከትሎ የተመሰረተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ከላይቤሪያ ጋር በመሆን መስራች ሀገር ናት ኢትዮጵያ እናም የተባበሩት መንግስታት ከተመሰረተ በኋላ ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ሙሉ ቁርጠኛ ሆና ቀጥላለች፡፡ የተ. ቻርተር መርሆ የሆነው የጋራ ደህንነት ለኢትዮጵያ ልዩ ትርጉም ያለው ነው ምክኒያቱም ያልተሳካው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ሙከራም ይሄው የዓለምን ሠላም ማስፈን ስለነበረ ነው፡፡ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ በድጋሚ ኢትዮጵያን ከፍሺት ኢጣሊያ ያልታደገበትን ሀላፊነቱን አስመልክተው የሚተቹበት ዝነኛ ንግግራቸው ኋላ ላይ ብዙዎች በዓለም አቀፍ መሰበረሰብ በጸጸት ሲከተላቸው ኖሯል፡፡

የጋራ ደህንነትና ትብብር ሀሳብ እንዲርቅ ያደረገውና የተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሠረት እንዲፈጠር ካደረጉ አንኳር ምክኒያቶች በእርግጥም አንዱ ይህ ነው፡፡

 Back to Home

የጎብኚዎች ብዛት
በዛሬ ቀን :   1091
በዚህ ሳምንት:   42703
በዚህ ወር:   13876
በዚህ ዓመት:   388909
አጠቃላይ ጎብኚዎች:    1230878
         ሚድያ

የሚለቀቁ ዜናዎችን ወዲያውኑ ለመመልከት