ክቡር አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን
ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ባንኮሌ ጋር ተወያይተዋል፡፡በወቅቱም ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ፣ ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳታ ይደርስ ዘንድ ምቹ ሁኔታ እየተደረገ እንደሆነ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርደር እንዲጀመር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለኮሚሽነሩ አብረራተዋል፡፡
የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ግሎባል ዴቨሎፕመንት ቪዥን ፕሬዝደንት ጋር ተወያይተዋል፡፡በወቅቱም በአገራችን እያካሄደ ያለውን የልማት ፕሮግራሞች አጠናክሮ እንዲቀጥል በተለይም በትምህረት ፣በጤና እና ግብርና ዘርፍ እያደረገ ያለውን አበረታች ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በአገሪቱ በድርቅና በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች ለመርዳት መንግስት የተለያዩ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህ ችግር ድርጅታቸው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የእስራኤል የፓርላማ አባላትን እና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በጎንደር የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል ፡፡ በጉብኝቱም በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ድጋፍ እንዲሰጡ በውይይተ ተነስቷል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች፡፡
በደቡብ አፍሪካ World Travel Market Africa የቱሪዝም ፕሮሞሽን ኤግዝቢሽን እንዲሁም ከዚሁ ጎን ለጎን በተካሄደው የአፍሪካ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተሳትፎ በማድረግ ፤ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት የሆኑ በቱሪዝም ልማት የተመረጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አስተዋወቋል።
ከሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ዜጎች መካከል ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
በፈረንሳይ “እኔም ለአገሬ" በሚል የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የመረዳጃ ማህበር ለተፈናቀሉ ዜጎች አስር ሺህ ዩሮ ድጋፍ አሰባስቧል።
በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 32 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፣በኩዌት ከዲፖርቴሽንና ከሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረ እና ከ100 በላይ ሰነድ አልባ ዜጎች ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
4. የኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤት የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ
በለንደን ኤምባሲያችን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲገነባ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል፡፡
በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡
በጊኒ ቢሳው የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር መላኩ ለገሰ የሹመት ደብዳቤ ቅጃቸውን ለጊኒ ቢሳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለማቅረባቸው እና መሠል ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃኑ መግለጫ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።