ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ሳምንት በተከናወኑ የዲፕሎሚሲ ሥራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጡ


(ሚያዝያ 13 ቀን 2014ዓ/ም አዲስ አበባ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንቱ በፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ክቡር አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል
1) በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፦
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን
ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ባንኮሌ ጋር ተወያይተዋል፡፡በወቅቱም ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ፣ ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳታ ይደርስ ዘንድ ምቹ ሁኔታ እየተደረገ እንደሆነ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርደር እንዲጀመር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለኮሚሽነሩ አብረራተዋል፡፡
የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ግሎባል ዴቨሎፕመንት ቪዥን ፕሬዝደንት ጋር ተወያይተዋል፡፡በወቅቱም በአገራችን እያካሄደ ያለውን የልማት ፕሮግራሞች አጠናክሮ እንዲቀጥል በተለይም በትምህረት ፣በጤና እና ግብርና ዘርፍ እያደረገ ያለውን አበረታች ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በአገሪቱ በድርቅና በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች ለመርዳት መንግስት የተለያዩ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህ ችግር ድርጅታቸው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የእስራኤል የፓርላማ አባላትን እና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በጎንደር የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል ፡፡ በጉብኝቱም በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ድጋፍ እንዲሰጡ በውይይተ ተነስቷል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች፡፡
2.ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ
በደቡብ አፍሪካ World Travel Market Africa የቱሪዝም ፕሮሞሽን ኤግዝቢሽን እንዲሁም ከዚሁ ጎን ለጎን በተካሄደው የአፍሪካ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተሳትፎ በማድረግ ፤ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት የሆኑ በቱሪዝም ልማት የተመረጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን አስተዋወቋል።
3.የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ፣
ከሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ዜጎች መካከል ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
በፈረንሳይ “እኔም ለአገሬ" በሚል የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የመረዳጃ ማህበር ለተፈናቀሉ ዜጎች አስር ሺህ ዩሮ ድጋፍ አሰባስቧል።
በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 32 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፣በኩዌት ከዲፖርቴሽንና ከሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረ እና ከ100 በላይ ሰነድ አልባ ዜጎች ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
4. የኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤት የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ
በለንደን ኤምባሲያችን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲገነባ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል፡፡
በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሁለተኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡
በጊኒ ቢሳው የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር መላኩ ለገሰ የሹመት ደብዳቤ ቅጃቸውን ለጊኒ ቢሳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለማቅረባቸው እና መሠል ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃኑ መግለጫ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Back to Home

More Trade Events ..

ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ሳምንት በተከናወኑ የዲፕሎሚሲ ሥራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጡ Read More


የኢትዮጵያ መንግሥት በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ ኢትዮጵያዊያን ለሩስያ ጦር ኃይል እየተመለመሉ ነው በሚል የወጣውን መሠረተ ቢስ መረጃ አስመልክቶ ላወጣው መግለጫ ምስጋና አቀረበ። Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሳምንቱ በተከናወኑ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። Read More


Press Briefing Summary 29 April 2022 Read More


The spokesperson of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Ambassador Dina Mufti, gave the Ministry’s biweekly press briefing today (April 21, 2022) to the media Read More


The Government of Ethiopia welcomes the Statement issued by the Embassy of the Russian Federation in Addis Ababa refuting the unfounded reports of recruitment for the Russian Armed Forces Read More


The spokesperson of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Ambassador Dina Mufti, gave the Ministry’s biweekly press briefing today (April 14, 2022) to the media. Read More


Press Statement On the Joint Report of Amnesty International and Human Rights Watch Read More


Press Briefing Summary 24 March 2022 Read More


Updates on Humanitarian Assistance to the #Tigray Region Read More


Read More

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   1285
THIS WEEK:   60925
THIS MONTH:   316923
THIS YEAR:   2945241
TOTAL:    6172839
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Regions
      * Neighboring Countries
      * African Countries
      * Middle East Countries
      * Asia Countries
      * Europe Countries
      * United State of America
         Media