የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሳምንቱ በተከናወኑ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።



የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሳምንቱ በተከናወኑ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ክቡር አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ፦
1.ፖለቲካ ዲፕሎማሲ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ውይይት
አድርገዋል፡፡ በውይይቱ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በማጠናከር እና በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ሃሳብ
ተለዋውጠው፤ ካናዳ በG7 ባላት ቦታ በአገራቸን ላይ የሚደረጉ ጫናዎችን እንዲቃለሉ ድጋፍ
እንድታደርግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ለ. በዋና መ/ቤት
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ ከፍትህ ሚኒስትር ከክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር በመሆን ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ መንግስት እየወሰዳቸው የሚገኙትን እርምጃዎች ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ አስረድተዋል፡፡ በገለጻው መንግስት ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እየሰራ መሆኑን፤ በአንዳንድ ተቋማት የሚወጡ መግለጫዎች መሬት ላይ ያሉ ሀቆችን የሚቃረኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለሰብአዊነት ሲባል የተወሰደው ግጭት የማቆም ውሳኔ ውጤታማ ይሆን ዘንድ የህወሃት ቡድን ተባባር መሆኑን እንዳለበት ለዲፕሎማቱ ተጠቁሟል፡፡ በሌላ በኩል ተመድ ለብቻው የሚያደርገው የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ ፤ ውጤታማ እንደማይሆና ጠቀሜታ የሌለው መሆኑን ለዲፕሎማቶቹ ተገልጿዋል፡፡ በተያያዘም በአገሪቱ ያሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ብሄራዊ ምክክር ለማካሄድ ኮሚሽነሮችን በመሰየም ወደ ሥራ መገባቱን ባለሥልፃናጹ አስረድተዋል፡፡ በአውሮፓና ካናዳ የሚገኙ የሚሲዮን ተወካዮችና የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ተወካዮች ጋር ከኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የሚጠበቁ የአድቮኬሲና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች፣ በቅርቡ የታወጀው የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ አስፈላጊነት እና አንደምታዎቹ፣እንዲሁም በአሜሪካ ኮንግረስ የቀረቡት ሁለት ረቂቅ ህጎች በተመለከተ በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከደቡብ ኮርያ Deputy Minister for Overseas Resources and Consular Affairs ጋር በሁለትዮሽና እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ሀገራችን ከደቡብ ኮርያ ጋር በትብብር መሥራት በምትችልበት መስኮችና በሀገራችንና አለም አቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን ምልከታ እና ከደቡብ ኮርያ መንግስት ሀገራችን በፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲና ኢኮኖሚ ዘርፎች በሁለትዮሽና በባለብዙ ዘርፍ የምትሻውን ድጋፍና ትብብር በማንሳት ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በጎንደር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ተመሥርቷል፡፡የፐብሊክ ዲፕሎማሲ መደበኛውን ዲፕሎማሲ በመደገፍ ካለው ፋይዳ አንጻር በተለያዩ ዩኒቬርሲቲዎች ከዚህ ቀደም ተመሥርቷል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ብሮዲካስትንግ ኮሪፖሬሽን ጋር በመተባበር ሳምንታዊ ቴሌቪዝን ፕሮግራም ለማስተላለፍ ውል ተፈራርሟል፡፡
መ.የኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤት የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ፣
በቱሪክ አምባሳደር አደም መሃመድ የሀበሺታን ተማሪዎች ማህበር ተወካዮች ተቀብለው በኤምባሲው ጽ/ቤት ውይይት አድርገዋል፡፡
በቻይና አፍሪካ ሥልጣኔዎች ዙሪያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ‘መልካም አጋርነት ዘላቂ የሚሆነው በሁለቱም ወገኖች በኩል በመከባበር ላይ የተመሰረተ እኩል ሲኖር ነው’ በማለት ንግግር አድርገዋል፡፡
በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በወቅታዊ አገራችን እና አፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ በፓሪስ አምባሳደር ሄኖክ ሻውል በፓን -አፍሪካንዝም እንቅስቀሴ እና በታለቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለፈረንሳይ ሰልጣኝ ዲፕሎማት ማብራሪያ ሰጥተዋል፣
በደቡብ ሱዳን ለሰልጣን ዲፕሎማቶች በታላቁ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ አምባሳደር ነቢል ገለጻ ሰትዋል|፡፡
2.ኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ
በበርሊን -ጀርመን የአትልክትና ፍራፍሬ ኤግዚቢሽኖች ላይ በመሳተፍ በአትክልትና ፍራፍሬ ያላትን አቅም ማስተዋወቅ ተችሏል፤
ኒውደልሂ የሚገኘው ሚሲዮናችን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በህንድ 3 የቢዝነስ ፕሮሞሽን ፎረሞችን በማዘጋጀት የኢንቨስትመንት እድል በሀገራችን በፋርማሲዩቲካል፣ በቴክስታይልና ጋርመንት እንዲሁም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው የህንድ ኩባንያዎች ገለጻ ሰጥቷል፡፡
የቤጂንግ ኤምባሲ ከZhejiang Yaoheng photoelectric technology Co.,Ltd ኃላፊዎች ጋር ባካሄደው
ውይይት ኩባንያው በአገራችን ቀደም ብሎ በኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ ያለውን ኢንቨስትመንት በማስፋፋት በግብርና ዘርፍበ rapeseed ምርት በ40 ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ እና በዘይት ማቀነባበር ፋብሪካ ለመክፈት ፍላጎቱን መኖሩን በተደረገው ውይይት መረዳት ተችሏል፤በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በግጭት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል፣
3.የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ፣
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊውን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱ ሥራ እንደቀጠለ መሆኑን አንስተው እስካሁንም ከ7ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
በእስራኤል በአምስት ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ11 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ አሰባስበዋል፣በቤልጂየም በብራሴልስ፣ በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ፣በሮም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን HR 6600 እና S.3199ን በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል፣ “ከኢድ አስከ ኢድ ወደ አገር ቤት ” የጉዞ ጥሪን በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር መድረኮች ተካሂዷዋል፡፡
ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በእነዚህ እና መሰል ወቅታዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።




Back to Home

More Trade Events ..

ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ሳምንት በተከናወኑ የዲፕሎሚሲ ሥራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጡ Read More


የኢትዮጵያ መንግሥት በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ ኢትዮጵያዊያን ለሩስያ ጦር ኃይል እየተመለመሉ ነው በሚል የወጣውን መሠረተ ቢስ መረጃ አስመልክቶ ላወጣው መግለጫ ምስጋና አቀረበ። Read More


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል- አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሳምንቱ በተከናወኑ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። Read More


Press Briefing Summary 29 April 2022 Read More


The spokesperson of Foreign Affairs of Ethiopia, H.E. Ambassador Dina Mufti, gave the Ministry’s biweekly press briefing today (April 21, 2022) to the media Read More


Read More

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   9463
THIS WEEK:   72240
THIS MONTH:   170677
THIS YEAR:   2426193
TOTAL:    5653791
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Regions
      * Neighboring Countries
      * African Countries
      * Middle East Countries
      * Asia Countries
      * Europe Countries
      * United State of America
         Media